Loading
Singer
አዝ፦ የእግዚአብሔርን ፡ መኖር ፡ ሠማዩ ፡ ነገረኝ ፡ ምድሩ ፡ አወራኝ ቀኑ ፡ ምሽት ፡ ሲሆን ፡ ሌሊቱ ፡ ሲነጋ ፡ አረጋገጠልኝ ያለ ፡ የነበረ ፡ ደግሞም ፡ የሚኖረው ፡ ዘለዓለም ፡ በክብሩ ፍጥረታት ፡ በሙሉ ፡ ስለህልውናው ፡ ይመሰክራሉ (፪x) ለሚመረመር ፡ ለባዕድ ፡ አእምሮ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነገር በከንቱ ፡ መድከም ፡ መሆን ፡ ተላላ ፡ እጅግ ፡ መሞኘት ሳይዩ ፡ የሚያምኑ ፡ ብጹአን ፡ ሆኑ ለስሙ ፡ አምነው ፡ በቤቱ ፡ ጸኑ መዳን ፡ አገኙ ፡ ከሞት ፡ ተረፉ ከዚህ ፡ ዓለም ፡ ይልቅ ፡ ብዙ ፡ አተረፉ ለእኛ ፡ ለደካሞች ፡ ይሄ ፡ እውነት ፡ በራ ፡ ለእኛ ፡ ለምስኪኖች ለእኛ ፡ ለደካሞች ፡ ይሄ ፡ እውነት ፡ ታየ ፡ ለእኛ ፡ ለምስኪኖች አዝ፦ የእግዚአብሔርን ፡ መኖር ፡ ሠማዩ ፡ ነገረኝ ፡ ምድሩ ፡ አወራኝ ቀኑ ፡ ምሽት ፡ ሲሆን ፡ ሌሊቱ ፡ ሲነጋ ፡ አረጋገጠልኝ ያለ ፡ የነበረ ፡ ደግሞም ፡ የሚኖረው ፡ ዘለዓለም ፡ በክብሩ ፍጥረታት ፡ በሙሉ ፡ ስለህልውናው ፡ ይመሰክራሉ (፪x) ያወቀ ፡ ሊመስል ፡ ጠቢብ ፡ የሆነ ፡ እጅግ ፡ የላቀ ሰነፍ ፡ መሆኑን ፡ ከሰው ፡ ሊደብቅ ፡ ልቡ ፡ እያወቀ ምኞቱን ፡ ሊያደርግ ፡ አምላኩን ፡ ክዶ ከህሊና ፡ ሙግት ፡ ሊያመልጥ ፡ ፈልጐ ድፍረት ፡ ቢሞላው ፡ በውስጡ ፡ ክፉ ከንቱ ፡ ሃሳቡን ፡ አወራ ፡ አፉ ሞኞችና ፡ ድሆች ፡ እግዚአብሔር (፪x) ፡ ኧረ ፡ እንደው ፡ ይላሉ ብሎ ፡ ደመደመ ፡ ተስፋ ፡ ቢሶች ፡ ናቸው ፡ ጥበብን ፡ ስላጡ (፪x) ነፍሱ ፡ ጌታን ፡ ብትፈልገው ፡ እራሱን ፡ አምላክ ፡ አደረገው የእግዚአብሔር ፡ ፍጥረታት ፡ . (1) . በድፍረት ፡ ነው ፡ . (2) . ፡ ክህደቱ የወንዙ ፡ የተራራው ፡ የባሕር ፡ የውቅያኖስ ፈጣሪውን ፡ ያሳያል ፡ የፍጥረት ፡ ግርማ ፡ ሞገስ አለ ፡ ይላል ፡ እግዚአብሔር ፡ አሃ አለ ፡ ይላሉ ፡ እግዚአብሔር አለ ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔር ፡ ኦሆ አለ ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔር