Loading
Singer
ሰማያት ፡ ያንጠባጠቡት ፡ ዝናብ ፡ ቀላያትም ፡ የያዙት ፡ ውኃ የምድርን ፡ ዛፎች ፡ ባስተባብር ፡ በደን ፡ ያሉ ፡ በበረሃ አሃሃ ፡ ውኃው ፡ ቀለም ፡ ቢሆን ፡ አሃሃ ፡ ዛፉም ፡ ደግሞ ፡ ብዕር አሃሃ ፡ ሁለቱም ፡ ቢጣመሩ ፡ አሃሃ ፡ ክብርህን ፡ እንዲያወሩ አዝ፦ ብዕሬ ፡ እንኳን ፡ አንደበት ፡ ኖሮት ፡ ቢፈጠር ኧረ ፡ ስንቱን ፡ ስንቱን ፡ ይናገር ፡ ነበር (፪x) ተራ ፡ ንጉስ ፡ ቤት ፡ እንኳን ፡ ገብቼ ስለእርሱና ፡ ዘሩ ፡ ቀለሜን ፡ በከንቱ ፡ ጨርሼ ንጉሥ ፡ ዘውዱን ፡ ሲደፋ ፡ የጻፍኩት ፡ አኔው ፡ ሰምቼ ሲሻር ፡ ሲዋረድ ፡ ፡ ተረኩት ፡ ደግሞ ፡ መልሼ አሃሃ ፡ ሰልችቶኛል ፡ ስተርከው ፡ የምድሩን አሃሃ ፡ ግራ ፡ ይገባኝ ፡ ሲሾሙና ፡ ሲሻሩ አሃሃ ፡ ምን ፡ አለ ፡ ሰዎች ፡ የላዩን ፡ ብትጽፉብኝ አሃሃ ፡ የምድሩን ፡ ከማውራት ፡ መተረክ ፡ ብትገላግሉኝ አሃሃ ፡ ጥሜ ፡ እንዲረካ ፡ የልቤ ፡ እንዲደርስ አሃሃ ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ ቀለሜን ፡ ስለእርሱ ፡ ብጨርስ አዝ፦ ብዕሬ ፡ እንኳን ፡ አንደበት ፡ ኖሮት ፡ ቢፈጠር ኧረ ፡ ስንቱን ፡ ስንቱን ፡ ይናገር ፡ ነበር (፪x) ወዶ ፡ አፍቅሮ ፡ ሲያስብ ፡ ሰው ፡ በልቡ ይጠበብብኛል ፡ ለመግለፅ ፡ የውስጥ ፡ ሃሳቡ ወደድኩኝ ፡ ባለበት ፡ ቅፅበት ፡ ጠላሁ ደግሞ ፡ ይልብኛል ወረት ፡ ያለው ፡ ፍቅር ፡ ለእኔስ ፡ ግራ ፡ ገብቶኛል አሃሃ ፡ ሰልችቶኛል ፡ ስተርከው ፡ የምድሩን አሃሃ ፡ ግራ ፡ ይገባኛል ፡ ስዋደዱ ፡ ሲጣሉ አሃሃ ፡ ምን ፡ አለ ፡ ሰዎች ፡ የላዩን ፡ ብትጽፉብኝ አሃሃ ፡ የምድሩን ፡ ከማውራት ፡ መተረክ ፡ ብትገላግሉኘ አሃሃ ፡ ጥሜ ፡ እንዲረካ ፡ የልቤ ፡ እንዲደርስ አሃሃ ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ ቀለሜን ፡ ስለእርሱ ፡ ብጨርስ አዝ፦ ብዕሬ ፡ እንኳን ፡ አንደበት ፡ ኖሮት ፡ ቢፈጠር ኧረ ፡ ስንቱን ፡ ስንቱን ፡ ይናገር ፡ ነበር (፪x) ከድሮ ፡ ጀምሮ ፡ ሁኔታው ፡ የማይቀየር እንዳለ ፡ የነበረ ፡ እንዲሁ ፡ ደግሞ ፡ የሚኖር ጥንት ፡ ስለእርሱ ፡ የጻፍኩት ፡ ያው ፡ ነው ፡ አልቀየርኩት ከትውልድ ፡ ትውልድ ፡ ይሄው ፡ አሳለፍኩት አሃሃ ፡ ስለመለወጡ ፡ ሁሌ ፡ የማልሰጋበት አሃሃ ፡ ከሁሉ ፡ የተለየ ፡ ጽናትን ፡ ያየሁበት አሃሃ ፡ ብጀምር ፡ ላወራ ፡ ስለእርሱ ፡ መስሎኝ ፡ አንደሰው አሃሃ ፡ ቀለሜ ፡ አለቀ ፡ እንጂ ፡ እሱንማ ፡ መች ፡ ልጨርሰው አሃሃ ፡ ብቀጥል ፡ ላወራ ፡ ስለእርሱ ፡ መስሎኝ ፡ እንደሰው አሃሃ ፡ አኔ ፡ አለኩ ፡ እንጂ ፡ ዘመኑን ፡ መች ፡ ልጨርሰው አዝ፦ ብዕሬ ፡ እንኳን ፡ አንደበት ፡ ኖሮት ፡ ቢፈጠር ኧረ ፡ ስንቱን ፡ ስንቱን ፡ ይናገር ፡ ነበር (፪x)