Loading
Singer
አንተን ፡ ጠርቶ ፡ ማን ፡ አፈረ ተማምኖብህ ፡ ማን ፡ ከሰረ የተዘጋውን ፡ ትከፍታለህ የታሰረውን ፡ ትፈታለህ የታመመውን ፡ ታድናለህ የሞተውን ፡ ታስነሳለህ (ስልጣን ፡ ያንተ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ስልጣን ፡ የአንተ ፡ ስልጣን ፡ የአንተ ፡ ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ ስልጣን ፡ የአንተ) (፪x) ባሕር ፡ መክፈል ፡ ትችላለህ ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ ፡ ሁሉ ፡ በደጅህ በር ፡ ሲዘጋ ፡ ትመጣለህ ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ ፡ ሁሉ ፡ በደጅህ የችግረኛውን ፡ ጩኸት ፡ የምትሰማ ፡ የክፉ ፡ ቀን ፡ ወዳጅ ፡ ኢየሱስ ፡ ብርሃን ፡ በጨለማ ፡ እስከዛሬስ ፡ ማንን ፡ ጥለህ ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ ፡ ሁሉ ፡ በደጅህ ቢመኩብህ ፡ ታስመካለህ ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ ፡ ሁሉ ፡ በደጅህ (ቢመኩብህ ፡ ታስመካለህ) (፬x) አዝ አንተን ፡ ጠርቶ መርከቢቱ ፡ ስትናወጥ ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ ፡ ሁሉ ፡ በደጅህ ልብም ፡ ሲርድ፡ ሲንቀጠቀጥ ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ ፡ ሁሉ ፡ በደጅህ በድንገት ፡ ብቅ ፡ ብለህ ፡ ማዕበሉን ፡ ገሰጽከው ለአምላክነትህ ፡ ኢየሱስ ፡ ፍጥረት ፡ ምስክር ፡ ነው እኛንም ፡ ከሕይወት ፡ ማዕበል ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ ፡ ሁሉ ፡ በደጅህ ስንት ፡ ጊዜ ፡ አሳረፍከን ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ ፡ ሁሉ ፡ በደጅህ (ስንት ፡ ጊዜ ፡ እረዳኸን ፡ ስንት ፡ ጊዜ ፡ አሳረፍከን) (፪x) አዝ አንተን ፡ ጠርቶ የሞተው ፡ ሲታዘዝልህ ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ ፡ ሁሉ ፡ በደጅህ ታላቁ ፡ ሰው ፡ ሲሰግድልህ ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ ፡ ሁሉ ፡ በደጅህ በዝች ፡ አጭር ፡ ዕድሜ ፡ ብዙ ፡ ጊዜ ፡ አይተናል ሳይወድ ፡ በግዱ ፡ ፍጥረት ፡ ለአንተ ፡ ይገዛል ማንስ ፡ ሊቆም ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ ፡ ሁሉ ፡ በደጅህ ለሚያምኑበት ፡ የሚያኮራ ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ ፡ ሁሉ ፡ በደጅህ (ለሚያምኑበት ፡ የሚያኮራ) (፬x) አዝ አንተን ፡ ጠርቶ