Loading
Singer
ትላንትና ፡ ለሊቱን ፡ በሥጋዬ ፡ ጥሬያለሁ አሁን ፡ ግን ፡ መረቦቼን ፡ በቃልህ ፡ እጥላለሁ የበረከት ፡ አምላክ ፡ ሆይ ፡ ስታዘዘው ፡ ቃልህን ተትረፈረፍኩኝ ፡ ዛሬ ፡ አይቻለሁ ፡ ሃይልህን (፫x) አዝ፦ ስለዚህ ፡ ሁልጊዜ ፡ ዘምርልሃለሁ በምሥጋናህም ፡ ላይ ፡ ሌላ ፡ ጨምራለሁ በጥሩ ፡ የዜማ ፡ ቃል ፡ ፊትህ ፡ እጫወታለሁ አምላኬ ፡ ጌታዬ ፡ አመሰግናለሁ አምላኬ ፡ ጌታዬ ፡ ከፍ ፡ አደርግሃለሁ በዚህ ፡ ተራራ ፡ ታላቅ ፡ የሰባ ፡ ግብዣ ፡ እድርገህ በብዙ ፡ ታምራቶች ፡ በደመና ፡ ተገልጠህ ሌላውን ፡ አስክረሳ ፡ አስክመርጥ ፡ በዚህ ፡ መኖር በብዙ ፡ ባርከኸኛል ፡ እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ ክበር (፫x) አዝ፦ ስለዚህ ፡ ሁልጊዜ ፡ ዘምርልሃለሁ በምሥጋናህም ፡ ላይ ፡ ሌላ ፡ ጨምራለሁ በጥሩ ፡ የዜማ ፡ ቃል ፡ ፊትህ ፡ እጫወታለሁ አምላኬ ፡ ጌታዬ ፡ አመሰግናለሁ አምላኬ ፡ ጌታዬ ፡ ከፍ ፡ አደርግሃለሁ በትሬን ፡ ብቻ ፡ ይዤ ፡ ተሻገርኩ ፡ ዪርዳኖስን የሁለት ፡ ክፍል ፡ ሰራዊት ፡ አርገኸኛል ፡ ዛሬ ፡ ግን በጠላት ፡ ፊት ፡ ለፊት ፡ በዘይት ፡ ቀብተህ ፡ እራሴን ላመላለስከኝ ፡ ጌታ ፡ ምን ፡ እላለሁ ፡ ተመስገን (፫x) አዝ፦ ስለዚህ ፡ ሁልጊዜ ፡ ዘምርልሃለሁ በምሥጋናህም ፡ ላይ ፡ ሌላ ፡ ጨምራለሁ በጥሩ ፡ የዜማ ፡ ቃል ፡ ፊትህ ፡ እጫወታለሁ አምላኬ ፡ ጌታዬ ፡ አመሰግናለሁ አምላኬ ፡ ጌታዬ ፡ ከፍ ፡ አደርግሃለሁ በዚያ ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ ላይ ፡ ብቻዬን ፡ ሳለሁኝ በድንገት ፡ ከአጠገቤ ፡ ምንጩ ፡ ፈለቀልኝ አለቆች ፡ እየቆፈሩ ፡ በቀራንዮ ፡ መስቀል ፡ ላይ የዘላለም ፡ ሕይወት ፡ ምንጭ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ኤልሻዳይ (፫x) አዝ፦ ስለዚህ ፡ ሁልጊዜ ፡ ዘምርልሃለሁ በምሥጋናህም ፡ ላይ ፡ ሌላ ፡ ጨምራለሁ በጥሩ ፡ የዜማ ፡ ቃል ፡ ፊትህ ፡ እጫወታለሁ አምላኬ ፡ ጌታዬ ፡ አመሰግናለሁ አምላኬ ፡ ጌታዬ ፡ ከፍ ፡ አደርግሃለሁ በኤማኦስ ፡ መንገድ ፡ ላይ ፡ ተስፋ ፡ ቆርጠን ፡ ሳለን ኢየሱስ ፡ እራሱ ፡ ቀድሞ ፡ ይሄድ ፡ ነበር ፡ አብሮን የልብን ፡ ሃዘን ፡ ነቅሎ ፡ ለሚሞላን ፡ በደስታ ምሥጋና ፡ ያንስብናል ፡ ለአምላካችን ፡ ለጌታ (፫x) አዝ፦ ስለዚህ ፡ ሁልጊዜ ፡ ዘምርልሃለሁ በምሥጋናህም ፡ ላይ ፡ ሌላ ፡ ጨምራለሁ በጥሩ ፡ የዜማ ፡ ቃል ፡ ፊትህ ፡ እጫወታለሁ አምላኬ ፡ ጌታዬ ፡ አመሰግናለሁ አምላኬ ፡ ጌታዬ ፡ ከፍ ፡ አደርግሃለሁ መስሎኝ ፡ ነበረ ፡ ለእኔስ ፡ በጠላቴ ፡ የተረታሁ አቀበት ፡ ቁልቁለቱን ፡ ከቶ ፡ የማልወጣው ከፍጥረት ፡ የታወቀው ፡ በድንቅ ፡ በታምራቱ በብዙ ፡ ጥንቃቄው ፡ ጠብቆኛል ፡ በቤቱ አኑሮኛል ፡ በቤቱ ፡ አክርሞኛል ፡ በቤቱ አዝ፦ ስለዚህ ፡ ሁልጊዜ ፡ ዘምርልሃለሁ በምሥጋናህም ፡ ላይ ፡ ሌላ ፡ ጨምራለሁ በጥሩ ፡ የዜማ ፡ ቃል ፡ ፊትህ ፡ እጫወታለሁ አምላኬ ፡ ጌታዬ ፡ አመሰግናለሁ አምላኬ ፡ ጌታዬ ፡ ከፍ ፡ አደርግሃለሁ