Loading
Singer
አዝ፦ ስለተደረገልኝ ፡ በጐነት ጨምሬ ፡ ምለው ፡ ምንድን ፡ ነው ጨምሬ ፡ ምለው ፡ ምንድን ፡ ነው (፪x) ሥራህ ፡ ከአእምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው (፪x) አመሰግንሃለው (፮x) እንደ ፡ ባለማዕረግ ፡ ሰው ፡ ተመልክተኸኝ የማይገባኝን ፡ ክብርን ፡ ሰጥተኸኝ የርስትህ ፡ ተካፋይ ፡ የአንተው ፡ አደረከኝ ለዚህ ፡ ልታበቃኝ ፡ ታዲያ ፡ እኔ ፡ ማን ፡ ነኝ (፪x) አዝ፦ ስለተደረገልኝ ፡ በጐነት ጨምሬ ፡ ምለው ፡ ምንድን ፡ ነው ጨምሬ ፡ ምለው ፡ ምንድን ፡ ነው (፪x) ሥራህ ፡ ከአእምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው (፪x) አመሰግንሃለው (፮x) ማዕበሉ ፡ በዝቶብኝ ፡ እኔን ፡ ሲያንገላታኝ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ አልኩኝ ፡ ሥምህን ፡ ጠራሁኝ እጅህን ፡ ዘርግተህ ፡ በፀናችው ፡ ክንድህ ታደከኝ ፡ አዳንከኝ ፡ ተባረክ ፡ ልበልህ (፪x) አዝ፦ ስለተደረገልኝ ፡ በጐነት ጨምሬ ፡ ምለው ፡ ምንድን ፡ ነው ጨምሬ ፡ ምለው ፡ ምንድን ፡ ነው (፪x) ሥራህ ፡ ከአእምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው (፪x) አመሰግንሃለው (፮x) የተገለጠውን ፡ ፍቅርህን ፡ እያየሁ እንዳልተቀበለ ፡ እንዴት ፡ እሆናለሁ ምህረት ፡ ማዳንህን ፡ ሁሌ ፡ አወራለሁ አምላኬ ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ ፍፁም ፡ አምላክ ፡ ማነው (፪x) አዝ፦ ስለተደረገልኝ ፡ በጐነት ጨምሬ ፡ ምለው ፡ ምንድን ፡ ነው ጨምሬ ፡ ምለው ፡ ምንድን ፡ ነው (፪x) ሥራህ ፡ ከአእምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው (፪x) አመሰግንሃለው (፮x) በለቅሶ ፡ ሸለቆ ፡ በወሰንከው ፡ ስፍራ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ለእኔ ፡ በረከትህ ፡ በዛ ከኃይል ፡ ወደ ፡ ኃይል ፡ ያሸጋገርከኝ ሁሉ ፡ በአንተ ፡ ሆነልኝ ፡ ኧረ ፡ ምን ፡ ጐደለኝ (፪x) አዝ፦ ስለተደረገልኝ ፡ በጐነት ጨምሬ ፡ ምለው ፡ ምንድን ፡ ነው ጨምሬ ፡ ምለው ፡ ምንድን ፡ ነው (፪x) ሥራህ ፡ ከአእምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው (፪x) አመሰግንሃለው (፮x)