Loading
Singer
አዝ፦ ስለስምህ ፡ መልካምነት ፡ ማን ፡ ተናግሮ ፡ ይዘልቃል ከተባለው ፡ በጐነትህ ፡ ያልተባለው ፡ በዝቷል በሄድኩበት ፡ የምጠራው ፡ የአንተ ፡ ስምማ አጠገቤ ፡ ብቻ ፡ ሳይሆን ፡ ለሩቁም ፡ ይሰማ (፪x) ኢየሱስ (፪x) ፡ ባልንበት ፡ ኧረ ፡ ስንቱ ፡ ተሰራበት ማረኝ ፡ ብለው ፡ ያለቀሱ ፡ ስለስምህ ፡ ተፈወሱ (፪x) ስምህን ፡ ስጠራ ፡ ሁሌ ፡ የማስበው ትልቁ ፡ ተራራ ፡ ሜዳ ፡ እንደሚሆን ፡ ነው አክብደው ፡ ያዩትን ፡ የሕይወት ፡ መንገድ ስምህ ፡ ባለፈበት ፡ ማይሄደው ፡ ሲሄድ ኢየሱስ ፡ የነፍሴ ፡ መዳኛ ኢየሱስ ፡ የኑሮዬ ፡ ዳኛ ኢየሱስ ፡ የሕይወት ፡ አክሊሌ ኢየሱስ ፡ ሰማያዊ ፡ ክብሬ (፪x) አዝ፦ ስለስምህ ፡ መልካምነት ፡ ማን ፡ ተናግሮ ፡ ይዘልቃል ከተባለው ፡ በጐነትህ ፡ ያልተባለው ፡ በዝቷል በሄድኩበት ፡ የምጠራው ፡ የአንተ ፡ ስምማ አጠገቤ ፡ ብቻ ፡ ሳይሆን ፡ ለሩቁም ፡ ይሰማ (፪x) ኢየሱስ (፪x) ፡ ባልንበት ፡ ኧረ ፡ ስንቱ ፡ ተሰራበት ማረኝ ፡ ብለው ፡ ያለቀሱ ፡ ስለስምህ ፡ ተፈወሱ (፪x) የአንተን ፡ መልካምነት ፡ ይዩ ፡ ወንድሞቼ አላፈርኩምና ፡ ስምህን ፡ ጠርቼ በበጐ ፡ ተጠሪ ፡ ክፋት ፡ የማያውቀው መልካሙ ፡ እረኛ ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው ኢየሱስ ፡ የነፍሴ ፡ መዳኛ ኢየሱስ ፡ የኑሮዬ ፡ ዳኛ ኢየሱስ ፡ የሕይወት ፡ አክሊሌ ኢየሱስ ፡ ሰማያዊ ፡ ክብሬ (፪x) ኢየሱስ (፫x) ፡ ኢየሱስ ፡ ሰማያዊ ፡ ክብሬ ኢየሱስ ፡ የነፍሴ ፡ መዳኛ ኢየሱስ ፡ የኑሮዬ ፡ ዳኛ ኢየሱስ ፡ የሕይወት ፡ አክሊሌ ኢየሱስ ፡ ሰማያዊ ፡ ክብሬ ኢየሱስ (፭x)