Loading
Singer
አዝ፦ ስለ ፡ አምላክነትህ ፡ ስለ ፡ ጌትነትህ ስለ ፡ እጆችህ ፡ ስራ ፡ ባወራው ፡ ባወራ አያልቅ ፡ የአንተ ፡ ሥራ (፪x) አያልቅ ፡ የአንተ ፡ ስራ (፬x) ሰባቱን ፡ ከዋክብት ፡ ኦርዬንን ፡ የሰራ ጨለማውን ፡ ንጋት ፡ ብርሀን ፡ የሚያበራ ቀኑን ፡ አጨልሞ ፡ ሌሊት ፡ የሚያደርገው ስራው ፡ እንዲህ ፡ ያማረው ፡ ስሙ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነዉ (፪x) አዝ፦ ስለ ፡ አምላክነትህ ፡ ስለ ፡ ጌትነትህ ስለ ፡ እጆችህ ፡ ስራ ፡ ባወራው ፡ ባወራ አያልቅ ፡ የአንተ ፡ ሥራ (፪x) አያልቅ ፡ የአንተ ፡ ስራ (፬x) ውሆችን ፡ በእፍኙ ፡ የሰፈረ ፡ ጌታ ሰማይንም ፡ ደግም ፡ በስንዝር ፡ የለካ ኽረ ፡ እግዚአብሔርን ፡ የአማከረው ፡ ማነው ማስተዋሉ ፡ ረቂቅ ፡ ኃይሉ ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው (፪x) አዝ፦ ስለ ፡ አምላክነትህ ፡ ስለ ፡ ጌትነትህ ስለ ፡ እጆችህ ፡ ስራ ፡ ባወራው ፡ ባወራ አያልቅ ፡ የአንተ ፡ ሥራ (፪x) አያልቅ ፡ የአንተ ፡ ስራ (፬x) በዓመታት ፡ መሀል ፡ ስራን ፡ ትሰራለህ ሁኔታ ፡ አያግድህ ፡ ከሁኔታ ፡ በላይ ፡ ነህ አቤት ፡ ይሄ ፡ ጌታ ፡ እኔ ፡ የማመልከው ለዘላለም ፡ ነዋሪ ፡ መለወጥ ፡ የማያውቁው (፪x) ስለዚህ ፡ ላምልከው ፡ በሀሴት ፡ ውሰጥ ፡ ሆኜ የማይለወጠውን ፡ ስላገኘች ፡ ነፍሴ ከቤቱ ፡ በረከት ፡ ስለረካች ፡ ነፍሴ (፪x) ከእርሱ ፡ ሌላ ፡ አልፈልግም እርሱ ፡ ለእኔ ፡ ምኞቴ ፡ ነው ርሀቤም ፡ ጥማቴም ፡ የሆነው ከእርሱ ፡ ሌላ ፡ አልፈልግም እርሱ ፡ ለእኔ ፡ መሻቴ ፡ ነው ርሀቤም ፡ ጥማቴም ፡ የሆነው ርሀቤም ፡ ጥማቴም ፡ የሆነው (፲፮x)