Loading
Singer
እንደነጋልኝ ፡ አይቶ ፡ ጠላቴ ከበሮውን ፡ ጥሎ ፡ ሮጠ ፡ ከፊቴ ድሌን ፡ ለማየት ፡ አልቻለምና ተራመድኩበት ፡ ነጋልኝና (፪x) አዝ፦ የእኔ ፡ ጌታ ፡ በአንድ ፡ ቀን ፡ ጀንበር ፡ ታሪኬን ፡ ቀየርከው የእኔ ፡ ጌታ ፡ ሁሉን ፡ ውብ ፡ አድርገህ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ የሰራኸው ስላሰብከኝ ፡ ስለወደደከኝ ፡ ነው ፡ በቤትህ ፡ የቆምኩት ነግቶልኝ ፡ ነው ፡ በጉባኤ ፡ መሃል ፡ ለአንተ ፡ የዘመርኩት (፪x) ሚታመኑህን ፡ የምታኮራ ያልተጠበቀን ፡ ድንቅ ፡ የምትሰራ አይቼሃለሁ ፡ ስትታደገኝ ከጠላቴ ፡ ቀስት ፡ ስታስመልጠኝ (፪x) አዝ፦ የእኔ ፡ ጌታ ፡ በአንድ ፡ ቀን ፡ ጀንበር ፡ ታሪኬን ፡ ቀየርከው የእኔ ፡ ጌታ ፡ ሁሉን ፡ ውብ ፡ አድርገህ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ የሰራኸው ስላሰብከኝ ፡ ስለወደደከኝ ፡ ነው ፡ በቤትህ ፡ የቆምኩት ነግቶልኝ ፡ ነው ፡ በጉባኤ ፡ መሃል ፡ ለአንተ ፡ የዘመርኩት (፪x) በጠዋት ፡ ማታ ፡ ጠብቀኸኛል ከጐኔ ፡ አለህ ፡ ምን ፡ ያሰጋኛል ጽኑ ፡ ግንቤ ፡ ነህ ፡ በጠላቴ ፡ ፊት ከአንተ ፡ ጋር ፡ ሆኜ ፡ አላውቅም ፡ ሽንፈት (፪x) አዝ፦ የእኔ ፡ ጌታ ፡ በአንድ ፡ ቀን ፡ ጀንበር ፡ ታሪኬን ፡ ቀየርከው የእኔ ፡ ጌታ ፡ ሁሉን ፡ ውብ ፡ አድርገህ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ የሰራኸው ስላሰብከኝ ፡ ስለወደደከኝ ፡ ነው ፡ በቤትህ ፡ የቆምኩት ነግቶልኝ ፡ ነው ፡ በጉባኤ ፡ መሃል ፡ ለአንተ ፡ የዘመርኩት (፪x)