Loading
Singer
አዝ፦ ስላንተ ፡ ሲወራ ፡ ሲነገር ፡ ቢዋል ፡ ቢታደር የሚበቃ ፡ አይደለም ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ያረከው ፡ ነገር እንዲሁ ፡ ብቻ ፡ ልበል ፡ ተመስገን ቃላት ፡ አይገልጸውም ፡ ያረከውን ፡ ነገር (፪x) ሞቴ ፡ በሕይወት ፡ ተቀይሮልኛል ፡ ኑር ፡ ብለህ ፡ ፈቅደህልኛል በምድር ፡ በርዝመቷ ፡ በስፋቷ ፡ በላይ ፡ በላይ ፡ በከፍታ እንድወጣ ፡ እንድገባ ፡ ፈቅደህልኛል የሚይዘኝ ፡ የለም ፡ ከፊቴ ፡ ወጥተህልኛል (፪x) አዝ ፦ ስላንተ ፡ ሲወራ ፡ ሲነገር ፡ ቢዋል ፡ ቢታደር የሚበቃ ፡ አይደለም ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ያረከው ፡ ነገር እንዲሁ ፡ ብቻ ፡ ልበል ፡ ተመስገን ቃላት ፡ አይገልጸውም ፡ ያረግከውን ፡ ነገር (፪x) አርነት ፡ ነፃ ፡ ወጥቻለሁ ፡ እርሱ ፡ ለቅቆኝ ፡ ተለቅቄያለሁ አልሄድ ፡ ወደኋላ ፡ ወደፊት ፡ እራመዳለሁ እርሱ ፡ ከከፈተው ፡ አትገባም ፡ የሚለኝ ፡ ማነው ሸክሜን ፡ ጣለ ፡ ቀንበሬን ፡ ሰበረ ፣ እዳዬም ፡ በርሱ ፡ ተከፈለ አለኝ ፡ አልጥልህም ፡ አልተውህም ፣ ፍጹም ፡ ከእጄ ፡ አላወጣህም መርጬሃለሁ ፡ ምንም ፡ ነገር ፡ አያስፈራህም አዝ፦ ስላንተ ፡ ሲወራ ፡ ሲነገር ፡ ቢዋል ፡ ቢታደር የሚበቃ ፡ አይደለም ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ያረከው ፡ ነገር እንዲሁ ፡ ብቻ ፡ ልበል ፡ ተመስገን ቃላት ፡ አይገልጸውም ፡ ያረከውን ፡ ነገር (፪x) እየገባኝ ፡ መጣ ፡ አሁን ፡ እየተረዳሁ ፣ ነገሬ ፡ ሁሉ ፡ ባንተ ፡ ሰምሮ ፡ እያየሁ አጋጣሚ ፡ አይደለም ፡ ለካ ፡ ከላይ ፡ ታዞ ፡ ነው አርፌ ፡ እንድኖር ፡ ቀድሞ ፡ ስራዬን ፡ ሰርቶት ፡ ነው ከተመስገን ፡ ሌላ ፡ ታዲያ ፡ የምለው ፡ ምንድነው ተመስገን (፬x) የኔ ፡ ጌታ ፡ ተመስገን ተመስገን ፡ ላረግክልኝ ፡ ነገር (፬x)