Loading
Singer
ምንድን ፡ ነው ፡ የመኖር ፡ ትርጉሙ ፡ የሕይወት ፡ ጣዕሙ ምንድን ፡ ነው ፡ ሃብትን ፡ ማካበቱ ፡ ዓለምን ፡ ማትረፉ ምንድን ፡ ነው ፡ ክብር ፡ ዝና ፡ ማግኘት ፡ ፊደልን ፡ መቁጠሩ ምንድን ፡ ነው ፡ ውበት ፡ ወጣትነት ፡ ጉብዝናው ፡ ጥቅሙ አዝ፦ አንተን ፡ ካላከበሩ (፬x) አንተን ፡ ካላከበሩ (፬x) ምንድን ፡ ነው ፡ የቃል ፡ ዕውቀት ፡ እድገት ፡ የአገልግሎት ፡ ብዛት ምንድን ፡ ነው ፡ ቀን ፡ ከሌት ፡ መሮጡ ፡ ሰውን ፡ ለማስደሰት ምንድን ፡ ነው ፡ በሥጋ ፡ ለባሽ ፡ መከበር ቅዱሱ ፡ መንፈስህ ፡ ሳይኖር ምንድን ፡ ነው (፫x) አዝ፦ አንተን ፡ ካላከበሩ (፬x) አንተን ፡ ካላከበሩ (፬x) ምንድን ፡ ነው ፡ ስለእኔ ፡ ሳይሆን ምንድን ፡ ነው ፡ ሕይወቴ ፡ በሙሉ ፡ ካላከበረህ ፡ እንዲሁ ምንድን ፡ ነው ፡ መድከሚ ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ጥቅሙ ምንድን ፡ ነው ፡ አላማዬ ፡ ካልሆንከኝ ፡ ኢየሱስ ከንቱ ፡ ነው (፬x) ከንቱ ፡ ነው (፬x) አዝ፦ አንተን ፡ ካላከበሩ (ከንቱ ፡ ነው) (፬x) አንተን ፡ ካላከበሩ (ከንቱ ፡ ነው) (፬x)