Loading
Singer
ቃልህን ፡ ሰምቼ ፡ ሥራህን ፡ አይቼ አይኔ ፡ በርቶልኛል ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ እዚህም ፡ እዚያም ፡ አልልም ፡ ለቅቄህ ፡ አልሄድም በጥበቃህ ፡ ሥር ፡ ነኝ ፡ አልሻም ፡ ሌላውን (፫x) ኦሆ አዝ፦ ስላንተ ፡ ያወራሉ ፡ ሰው ፡ ሲናገር ፡ ስለሰሙ የሰው ፡ ስርዓት ፡ ወግ ፡ ልማዱ ፡ ሕይወት ፡ የለሽ ፡ አምልኮውን ኃይል ፡ ብርታቱን ፡ የከዳውን ፡ መች ፡ ሊገባኝ ፡ እርሱን ፡ ላየው በእውነት ፡ ልስገድ ፡ ለሚገባው ወደር ፡ መሳይ ፡ ለእኔ ፡ የለው በእውነት ፡ ላክብር ፡ ስለምወደው ኦሆ ለደካማው ፡ ብርታት ፡ ለዛለውም ፡ ጉልበት ማለምለምን ፡ ሚወድ ፡ ድንቅ ፡ መካር ፡ ሀያል ፡ ነው የኢየሱስ ፡ ከኔ ፡ ጋር ፡ ነው ፡ ማንን ፡ እፈራለሁ የሚያቆመኝ ፡ የለም ፡ ከፍ ፡ ብዬ ፡ እሄዳለሁ እንደ ፡ ንስር ፡ እወጣለሁ ከፍ ፡ ብዬ ፡ እሄዳለሁ ኦሆ አዝ፦ ስላንተ ፡ ያወራሉ ፡ ሰው ፡ ሲናገር ፡ ስለሰሙ የሰው ፡ ስርዓት ፡ ወግ ፡ ልማዱ ፡ ሕይወት ፡ የለሽ ፡ አምልኮውን ኃይል ፡ ብርታቱን ፡ የከዳውን ፡ መች ፡ ሊገባኝ ፡ እርሱን ፡ ላየው በእውነት ፡ ልስገድ ፡ ለሚገባው ወደር ፡ መሳይ ፡ ለእኔ ፡ የለው በእውነት ፡ ላክብር ፡ ስለምወደው ያማረ ፡ ዝማሬ ፡ ቅኔዬም ፡ ለእርሱ ፡ ነው ሁሉ ፡ ከእርሱ ፡ በእርሱ ፡ ለእርሱ ፡ ነው ፡ የምሰጠው በገና ፡ ልደርድር ፡ መሰንቆዬን ፡ ላንሳ የከንፈሬን ፡ ፍሬ ፡ ዜማዬን ፡ ላሰማ ምሥጋና ፡ ላሰማ ፡ ዜማዬን ፡ ላሰማ አዝ፦ ስላንተ ፡ ያወራሉ ፡ ሰው ፡ ሲናገር ፡ ስለሰሙ የሰው ፡ ስርዓት ፡ ወግ ፡ ልማዱ ፡ ሕይወት ፡ የለሽ ፡ አምልኮውን ኃይል ፡ ብርታቱን ፡ የከዳውን ፡ መች ፡ ሊገባኝ ፡ እርሱን ፡ ላየው በእውነት ፡ ልስገድ ፡ ለሚገባው ወደር ፡ መሳይ ፡ ለእኔ ፡ የለው በእውነት ፡ ላክብር ፡ ስለምወደው ፍሬ ፡ የለሽ ፡ ከንቱ ፡ ወሬ ፡ መች ፡ ኣውቃለሁ የአንተን ፡ ቃል ፡ በንፁህ ፡ ልብ ፡ እኔ ፡ አምናለሁ (፪x)