Loading
Singer
አዝ፦ ሠላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፍቅር ፡ ኢየሱስ ፡ ነው እረፍት ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ደስታ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፤ ኢየሱስ ፡ ነው (፫x) ለነገድ ፡ ለጐሳ ፡ ሠላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው በአገሮች ፡ መሃል ፡ ሠላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ለሰባቱ ፡ አህጉራት ፡ ሠላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ለዓለም ፡ በሙሉ ፡ ሠላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ከሰው ፡ ምን ፡ ይገኛል ፡ ሥጋ ፡ ከለበሰ ባንዱ ፡ ስናማርር ፡ ይመጣል ፡ የባሰ ይኸኛው ፡ ሲያጠራ ፡ ያኛው ፡ ሲያደፈርስ ባለንበት ፡ መሔድ ፡ ውኃ ፡ ቅዳ ፡ መልስ አንዴ ፡ ከጠጣን ፡ እንዳንጠማ የችግር ፡ ወሬ ፡ እንዳንሰማ ማረፍ ፡ ከፈለግን ፡ እስክወዲያኛው ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ የሰላም ፡ ዳኛው አዝ፦ ሠላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፍቅር ፡ ኢየሱስ ፡ ነው እረፍት ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ደስታ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፤ ኢየሱስ ፡ ነው (፫x) በቤተስብ ፡ መሃል ፡ሠላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ለባለትድሮች ፡ ሠላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ለወንድም ፡ ለሴትም ፡ ሠላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ለያንዳንዱ ፡ ሕይወት ፡ ሠላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ሠይጣን ፡ ጥላውን ፡ ሲጥል ፡ ገብቶ ፡ ሲያምታታ ቤተሰብ ፡ ሲበትን ፡ ትዳርን ፡ ሲፈታ ቤቶች ፡ ፈረሱና ፡ ተዘጉና ፡ ደጆች ጐዳናውን ፡ ሞሉት ፡ የመንገድ ፡ ዳር ፡ ልጆች ምስቅልቅል ፡ ላለ ፡ ሕብረተሰብ ሩቅ ፡ አያስኬድም ፡ መፍትሔው ፡ ቅርብ የጌታን ፡ መንግሥት ፡ ጽድቁን ፡ ብትሹ አሁን ፡ ይፈታል ፡ ዕንቆቅልሹ አዝ፦ ሠላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፍቅር ፡ ኢየሱስ ፡ ነው እረፍት ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ደስታ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፤ ኢየሱስ ፡ ነው (፫x) ማታ ፡ ስንተኛ ፡ ሠላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ጥዋት ፡ ስንነሣ ፡ ሠላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው በመንገድ ፡ ስንሔድ ፡ ሠላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው በሥራ ፡ በዕረፍት ፡ ሠላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው እስቲ ፡ ዕራስህን ፡ ባትደልል ፡ ምን ፡ አለ ጢርነቱ ፡ እንደሆን ፡ በልብህ ፡ ውስጥ ፡ አለ ሲጋራ ፡ ብታጨስ ፡ ጫትም ፡ ብትበላ ውስኪ ፡ ብትጠጣ ፡ አረቂና ፡ ጠላ መተንፈሻ ፡ ነው ፡ አፍንጫ ፡ አይደል ፡ ጭስ ፡ ማውጫ ሳንባ ፡ ሲቃጠል ፡ አንጀት ፡ ሲንጫጫ አበላሽቶታል ፡ ወዝብ ፡ ጠረንህ የሚያሳምር ፡ ኢየሱስ ፡ አለልህ አዝ፦ ሠላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፍቅር ፡ ኢየሱስ ፡ ነው እረፍት ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ደስታ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፤ ኢየሱስ ፡ ነው (፫x)