Loading
Singer
አዝ፦ ሰላም (፫x) ፡ ሰላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፪x) ደጁ ፡ ሳይከፈት ፡ ግድግዳው ፡ ሳይፈርስ የሰላሙ ፡ ጌታ ፡ ገባ ፡ ኢየሱስ ለተጨነቁቱ ፡ ግራ ፡ ለገባቸው ሰላም ፡ ለእናንተ ፡ ይሁን ፡ ብሎ ፡ አሳረፋቸው አዝ፦ ሰላም (፫x) ፡ ሰላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፪x) በጠመንጃ ፡ አፈ ፡ ሙዝ ፡ ወይ ፡ በእርቅ ፡ ድርድር የተገኘ ፡ ሰላም ፡ አላየንም ፡ በምድር ከዚህ ፡ የተቋጠረ ፡ ከዚያ ፡ ጋር ፡ ተፈታ ስላልቀደመ ፡ ነው ፡ የሰላሙ ፡ ጌታ አዝ፦ ሰላም (፫x) ፡ ሰላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፪x) የሃገር ፡ መሪዎች ፡ ክብር ፡ ሥልጣናቹህ የውክልና ፡ ነው ፡ ወዶ ፡ የሰጣችሁ ሞኝነት ፡ ቢመስልም ፡ ጌታን ፡ ተቀበሉ ህዝቡን ፡ እንድመራ ፡ እኔን ፡ ምራ ፡ በሉ አዝ፦ ሰላም (፫x) ፡ ሰላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፪x) አውራጃው ፡ ወረዳው ፡ ቀበሌም ፡ መንደሩ ንግዱም ፡ ሃይማኖቱም ፡ እድር ፡ ማህበሩም ምድር ፡ እንዲፈወስ ፡ አየር ፡ እንዲጠራ ሁሉም ፡ እጁን ፡ ያንሳ ፡ ኢየሱስን ፡ ይጥራ አዝ፦ ሰላም (፫x) ፡ ሰላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፪x) ምሁር ፡ ነህ ፡ ተማሪ ፡ ሃኪም ፡ ገበሬዉ ኢየሱስ ፡ ያድናል ፡ ጥሪው ፡ ላንተም ፡ ነው የትዳርህ ፡ ኪዳን ፡ ጐጆህ ፡ አይፍረስ የሰላሙ ፡ ሉዑል ፡ በቤትህ ፡ ይንገሥ አዝ፦ ሰላም (፫x) ፡ ሰላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፪x) መጠጥና ፡ ዘፈን ፡ ጐበዝና ፡ ቆንጆው አቃወሰህ ፡ ጤናህ ፡ አፈረሰ ፡ ጐጆው ደግሞ ፡ የእሳት ፡ ፍርድ ፡ አለ ፡ ከዚህ ፡ የባሰዉ የአምላክ ፡ ጥሪ ፡ ሰምቶ ፡ ላልተመለሰው አዝ፦ ሰላም (፫x) ፡ ሰላም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፪x)