Loading
Singer
ቅብዝብዝነትን ፡ አጣሁት ፡ ከላዬ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ገዛው ፡ ዘልቆ ፡ ልቦናዬን ኃይልን ፡ ከአርያም ፡ መልበሴን ፡ የማውቀው የማያልፍ ፡ ሰላም ፡ ስላልተለየኝ ፡ ነው አዝ፦ ሰላም ፡ አለኝ ፡ እንደወንዝ ፡ እንደወንዝ ፡ የሚፈስ አዕምሮዬን ፡ የሚያረሰርስ ደስታ ፡ አለኝ ፡ ከውስጤ ፡ ከውስጤ ፡ ማይጠፋ ኢየሱስ ፡ ክብሩ ፡ ይስፋ ፡ ኡ.... (፪x) ማነው ፡ የሚነጥቀኝ ፡ ይህንን ፡ ጸጥታ የማይለየኝ ፡ ከውስጤ ፡ ለአንድ ፡ አፍታ ከሰማይ ፡ ተገኝቶ ፡ ሰማያዊ ፡ የሆነ ምድራዊማ ፡ ይሄኔ ፡ ትቶኝ ፡ በተነነ አዝ፦ ሰላም ፡ አለኝ ፡ እንደወንዝ ፡ እንደወንዝ ፡ የሚፈስ አዕምሮዬን ፡ የሚያረሰርስ ደስታ ፡ አለኝ ፡ ከውስጤ ፡ ከውስጤ ፡ ማይጠፋ ኢየሱስ ፡ ክብሩ ፡ ይስፋ ፡ ኡ.... (፪x) እግዚአብሔር ፡ ይመስገን ፡ እንቅልፌን ፡ እተኛለሁ አደራዬን ፡ ለእርሱ ፡ ለአምላኬ ፡ እጥላለሁ የብረት ፡ መዝጊያዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆኖልኛል በእርሱ ፡ ተሸሽጌ ፡ ምንስ ፡ ይደፍረኛል አዝ፦ ሰላም ፡ አለኝ ፡ እንደወንዝ ፡ እንደወንዝ ፡ የሚፈስ አዕምሮዬን ፡ የሚያረሰርስ ደስታ ፡ አለኝ ፡ ከውስጤ ፡ ከውስጤ ፡ ማይጠፋ ኢየሱስ ፡ ክብሩ ፡ ይስፋ ፡ ኡ.... (፪x) ጌታ ፡ መሰረቴ ፡ የማይነቃነቅ ድጋፍ ፡ መጽንናኛዬ ፡ የሚያነሳኝ ፡ ስወድቅ መናወጥ ፡ ከልቤ ፡ ጠፍቷል ፡ ላይመለስ የሰላሜ ፡ ጌታ ፡ ይመስገን ፡ ኢየሱስ አዝ፦ ሰላም ፡ አለኝ ፡ እንደወንዝ ፡ እንደወንዝ ፡ የሚፈስ አዕምሮዬን ፡ የሚያረሰርስ ደስታ ፡ አለኝ ፡ ከውስጤ ፡ ከውስጤ ፡ ማይጠፋ ኢየሱስ ፡ ክብሩ ፡ ይስፋ ፡ ኡ.... (፫x)