Loading
Singer
አዝ፦ ሰላም ፡ አለኝ (፫x) ፡ በልቤ ፡ በልቤ ቅዱስ ፡ ቃሉን ፡ አንብቤ ፡ ደህንነት ፡ አግኝቻለሁ በጌታ ፡ ሰላም ፡ አግኝቻለሁ ሰላሜ ፡ በውስጤ ፡ እንዲህ ፡ የፈሰሰው ኢየሱስ ፡ በደሙ ፡ ሕይወቴን ፡ ገዝቶት ፡ ነው በጭንቅ ፡ ከመወጠር ፡ አዕምሮዬ ፡ ያረፈው እረፍት ፡ የሚሰጠው ፡ ጌታ ፡ ስላለኝ ፡ ነው ባይሆንማ ፡ ኢየሱስ ፡ ለእኔ ፡ ባይኖርልኝ ሕይወቴን ፡ ባይገዛው ፡ ባይቆጣጠረኝ በጭንቀት ፡ ተይቬ ፡ ጉስቁልና ፡ ከቦኝ በስቃይ ፡ ተውጬ ፡ ነበረ ፡ የምገኝ ግን ፡ ጌታዬ ፡ ኢየሱስ ፡ እርሱ ፡ ስላለልኝ እረፍት ፡ አግኝቻለሁ ፡ ተፈትቻለሁኝ (፪x) አዝ፦ ሰላም ፡ አለኝ (፫x) ፡ በልቤ ፡ በልቤ ቅዱስ ፡ ቃሉን ፡ አንብቤ ፡ ደህንነት ፡ አግኝቻለሁ በጌታ ፡ ሰላም ፡ አግኝቻለሁ ልቤ ፡ መልካም ፡ ነገር ፡ እንዲህ ፡ ያፈለቀው የእግዚአብሔር ፡ ሃሳብ ፡ ሕይወቴን ፡ ሞልቶት ፡ ነው ልቤን ፡ ለእርሱ ፡ አርፎ ፡ ተዋርዶ ፡ የተገዛው እውነተኛ ፡ ፍቅሩን ፡ አውቆ ፡ ተረድቶት ፡ ነው ሕይወቴ ፡ ነው ፡ ነው ፡ ሰላሜ ፡ ነው ፡ ነው እረፍቴ ፡ ነው ፡ ነው ፡ አቅሜ ፡ ነው የምመካበት ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ አለ ለእኔስ ፡ ኢየሱሴ ፡ ካለ ባይሆንማ ፡ ኢየሱስ ፡ ለእኔ ፡ ባይኖርልኝ ሕይወቴን ፡ ባይገዛው ፡ ባይቆጣጠረኝ በጭንቀት ፡ ተይቬ ፡ ጉስቁልና ፡ ከቦኝ በስቃይ ፡ ተውጬ ፡ ነበረ ፡ የምገኝ ግን ፡ ጌታዬ ፡ ኢየሱስ ፡ እርሱ ፡ ስላለልኝ እረፍት ፡ አግኝቻለሁ ፡ ተፈትቻለሁኝ (፪x) በጤንነት ፡ ሆኜ ፡ መውጣቴ ፡ መግባቴ ኢየሱስ ፡ ሆኖልኝ ፡ ነው ፡ ኃይልና ፡ ጉልበቴ ወደ ፡ መልካም ፡ ስፍራ ፡ እግሬ ፡ የሚሮጠው እግሬን ፡ የሚመራ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆኖ ፡ ነው ሕይወቴ ፡ ነው ፡ ነው ፡ ፈዋሼ ፡ ነው ፡ ነው እረፍቴ ፡ ነው ፡ ነው ፡ አቅሜ ፡ ነው የምመካበት ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ አለ ለእኔስ ፡ ኢየሱሴ ፡ ካለ ባይሆንማ ፡ ኢየሱስ ፡ ለእኔ ፡ ባይኖርልኝ ሕይወቴን ፡ ባይገዛው ፡ ባይቆጣጠረኝ በጭንቀት ፡ ተይቬ ፡ ጉስቁልና ፡ ከቦኝ በስቃይ ፡ ተውጬ ፡ ነበረ ፡ የምገኝ ግን ፡ ጌታዬ ፡ ኢየሱስ ፡ እርሱ ፡ ስላለልኝ እረፍት ፡ አግኝቻለሁ ፡ ተፈትቻለሁኝ (፪x) አቅሜ ፡ የእርሱን ፡ ስራ ፡ እንዴት ፡ ሊናገረው የእርሱ ፡ ውለታ ፡ በልቤ ፡ ሞልቶ ፡ ነው ልቤም ፡ መስቀሉ ፡ ስር ፡ ስለተዋረደ የእግዚአብሔር ፡ መንፈስ ፡ በውስጤ ፡ ነደደ ባይሆንማ ፡ ኢየሱስ ፡ ለእኔ ፡ ባይኖርልኝ ሕይወቴን ፡ ባይገዛው ፡ ባይቆጣጠረኝ በጭንቀት ፡ ተይቬ ፡ ጉስቁልና ፡ ከቦኝ በስቃይ ፡ ተውጬ ፡ ነበረ ፡ የምገኝ ግን ፡ ጌታዬ ፡ ኢየሱስ ፡ እርሱ ፡ ስላለልኝ እረፍት ፡ አግኝቻለሁ ፡ ተፈትቻለሁኝ (፪x) አዝ፦ ተለወጥኩኝ (፫x) ፡ በኢየሱስ ፡ በኢየሱስ አዲስ ፡ ፍጥረት ፡ ሆኛለሁ መንፈሱን ፡ አግኝቻለሁ በጌታ ፡ ለውጥን ፡ አግኝቻለሁ የእግዚአብሔር ፡ ማዳን ፡ ለሰው ፡ የማወራው ማዳኑን ፡ በዐይኔ ፡ ስለአየሁኝ ፡ ነው ሰዎችን ፡ ለመውደድ ፡ ለማፍቀር ፡ የቻልኩት በጌታዬ ፡ ፍቅር ፡ ስላገኘውሁ ፡ ነው ፡ እረፍት እረፍት ፡ አለኝ (፫x) ፡ በኢየሱስ ፡ በኢየሱስ የማይጠፋ ፡ ደስታ ፡ የማይለወጥ ፡ ተስፋ በሕይወቴ ፡ በጣም ፡ ተስፋፋ ባይሆንማ ፡ ኢየሱስ ፡ ለእኔ ፡ ባይኖርልኝ ሕይወቴን ፡ ባይገዛው ፡ ባይቆጣጠረኝ በጭንቀት ፡ ተይቬ ፡ ጉስቁልና ፡ ከቦኝ በስቃይ ፡ ተውጬ ፡ ነበረ ፡ የምገኝ ግን ፡ ጌታዬ ፡ ኢየሱስ ፡ እርሱ ፡ ስላለልኝ እረፍት ፡ አግኝቻለሁ ፡ ተፈትቻለሁኝ (፪x) ሕይወቴ ፡ ነው ፡ ነው ፡ ፈዋሼ ፡ ነው ፡ ነው እረፍቴ ፡ ነው ፡ ነው ፡ አቅሜ ፡ ነው የምመካበት ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ አለ ለእኔስ ፡ ኢየሱሴ ፡ ካለ