Loading
Singer
ለምንስ ፡ እፈራለሁ ፡ ኧረ ፡ ለምን ፡ እሰጋለሁ ታዲያ ፡ ለምን ፡ እፈራለሁ ፡ እኮ ፡ ለምን ፡ እሰጋለሁ አዝ፦ አምላኬ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ነው አይተወኝ ፡ እሱ ፡ ታማኝ ፡ ነው ሥጋቴ ፡ ኧረ ፡ ለምኔ ተዋጊው ፡ እያለ ፡ ጐኔ ዘለዓለሜን ፡ ይዞታል ፡ ከቶ ፡ አትፍራ ፡ ብሎኛል አሳርፎኝ ፡ በጉያው ፡ ስር ፡ ልምን ፡ ልፍራ ፡ እንዴት ፡ ልሸበር በእጁ ፡ መዳፍ ፡ ቀርጾኛል ፡ አበጃጅቶ ፡ ሰርቶኛል አንተ ፡ የእኔ ፡ ብሎኛል ፡ ሥጋት ፡ የለኝ ፡ አሳርፎኛል አዝ፦ አምላኬ/የጠራኝ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ነው አይተወኝ ፡ እሱ ፡ ታማኝ ፡ ነው ሥጋቴ ፡ ኧረ ፡ ለምኔ ተዋጊው ፡ እያለ ፡ ጐኔ (፪x) የእኔ ፡ ነገር ፡ በእጁ ፡ ላይ ፡ ነው ሊያደርገው ፡ የታመነ ፡ ነው አላማዉም ፡ ከእንግዲህማ ቀን ፡ ቆጥሯል ፡ እሱ ፡ ሊመጣ በጊዜው ፡ ሁሉ ፡ ሆኖ ነገሬ ፡ በጌታ ፡ ሰምሮ አያለሁ ፡ ፍርሃቴ ፡ ይብቃ ቃል ፡ ወጥቷል ፡ ከቸሩ ፡ ጌታ ቃል ፡ እያለኝ ፡ ለምን ፡ እፈራለሁ የልጅነት ፡ ስልጣን ፡ የእኔ ፡ ነው ወጀቡንም ፡ በድል ፡ አዘዋለሁ አትፍራ ፡ ያለኝ ፡ ጌታ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ነው በቃ ፡ ልረፍ ፡ ከእንግዲህ ፡ ሳልሰጋ የታምንኩት ፡ አለ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ሁሉን ፡ ትቼ ፡ ሁሉን ፡ ለእርሱ ፡ ጥዬ ያለፍርሃል ፡ ልኑር ፡ . (1) . አዝ፦ የጠራኝ/አምላኬ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ነው አይተወኝ ፡ እሱ ፡ ታማኝ ፡ ነው ሥጋቴ ፡ ኧረ ፡ ለምኔ ተዋጊው ፡ እያለ ፡ ጐኔ (፪x)