Loading
Singer
እግሮችም ፡ የሉኝም ፡ ፊትህ ፡ የምቆምበት ዓይኖችም ፡ የሉኝም ፡ አንተን ፡ የማይበት የጠራኸኝ ፡ አምላክ ፡ ውርደቴን ፡ ተመልከት ከገባሁበት ፡ ማጥ ፡ አውጣኝ ፡ በአንተ ፡ ምህረት አዝ፦ ስብራቴ ፡ የማይፈወስ ፡ ይመስላል መደኃኒቴ ፡ አንተ ፡ ግን ፡ ምን ፡ ይሳንሃል ምህረትህ ፡ ካለ ፡ ማጉረምረም ፡ ምን ፡ ይጠቅመኛል በእጅህ ፡ ውስጥ ፡ መውደቅ ፡ ኦ ፡ እጅግ ፡ ይሻለኛል ከአንተ ፡ የተሰወረ ፡ ምን ፡ አለ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፍፁም ፡ ሳይገለጽ ፡ ተደብቆ ፡ የሚቆይ የልቤ ፡ መርማሪ ፡ የእኔ ፡ ውስጥ ፡ አዋቂ ጉድለቴን ፡ ይቅር ፡ በል ፡ የነፍሴ ፡ ጠባቂ አዝ፦ ስብራቴ ፡ የማይፈወስ ፡ ይመስላል መደኃኒቴ ፡ አንተ ፡ ግን ፡ ምን ፡ ይሳንሃል ምህረትህ ፡ ካለ ፡ ማጉረምረም ፡ ምን ፡ ይጠቅመኛል በእጅህ ፡ ውስጥ ፡ መውደቅ ፡ ኦ ፡ እጅግ ፡ ይሻለኛል ምንም ፡ ቸር ፡ ብትሆን ፡ በአንተ ፡ አይዘበትም ጉዴን ፡ ለመሸፈን ፡ ምክንያት ፡ አላቀርብም ያው ፡ ከነበደሌ ፡ ራሴን ፡ ሰጥቻለሁ ምረህ ፡ ተቀበለኝ ፡ ቃልህን ፡ ጥሻለሁ አዝ፦ ስብራቴ ፡ የማይፈወስ ፡ ይመስላል መደኃኒቴ ፡ አንተ ፡ ግን ፡ ምን ፡ ይሳንሃል ምህረትህ ፡ ካለ ፡ ማጉረምረም ፡ ምን ፡ ይጠቅመኛል በእጅህ ፡ ውስጥ ፡ መውደቅ ፡ ኦ ፡ እጅግ ፡ ይሻለኛል ምንም ፡ እንኳን ፡ ዛሬ ፡ ሃፍረት ፡ ቢሸፍነኝ ፊትህን ፡ ለማየት ፡ ከቶ ፡ ቢያዳግተኝ በተስፋ ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ ቀኔን፡ ጠብቃለሁ በድል ፡ ልታድሰኝ ፡ እንደምትችል ፡ አምናለሁ አዝ፦ ስብራቴ ፡ የማይፈወስ ፡ ይመስላል መደኃኒቴ ፡ አንተ ፡ ግን ፡ ምን ፡ ይሳንሃል ምህረትህ ፡ ካለ ፡ ማጉረምረም ፡ ምን ፡ ይጠቅመኛል በእጅህ ፡ ውስጥ ፡ መውደቅ ፡ ኦ ፡ እጅግ ፡ ይሻለኛል