Loading
Singer
ውስጤን ፡ ዝም ፡ ብሎ ፡ ይለኛል ፡ ደስ ፡ ደስ ፡ ደስ ፡ ደስ (X ፪) ምን ፡ ሆነህ ፡ ነው ፡ ካሉኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ማን ፡ አገኘህ ፡ ላሉኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ሰላሜማ ፡ ደስታዬማ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ለኔ ምንም ፡ ነገር ፡ የማይተካው ፡ ነው ፡ የዘላለሜ (ሳየው ፡ ካጎነበስኩበት ፡ ሳየው ፡ ቀና ፡ ቀና ፡ እላለሁ ሳየው ፡ ምርኮ ፡ እንዳገኘ ፡ ሰው ፡ ሳየው ፡ በፊቱ ፡ እዘላለሁ) ፡ X ፪ ሳየው ፡ ሳየው ፡ ሳየው (፪) ሁልጊዜ ፡ ሳዝን ፡ ስተክዝ ፡ የሚያውቁኝ ሀዘኔ ፡ ተገፍፎ ፡ ደስ ፡ ብሎኝ ፡ አገኙኝ እጅጉን ፡ ተገርመው ፡ አይን ፡ አይኔን ፡ ፡ እያዩኝ ምን ፡ ብታገኝ ፡ ነው ፡ ደስ ፡ ያለህ ፡ እያሉ ብር ፡ ነው? ወርቅ ፡ ነው? ምስጢሩን ፡ ንገረን እንዲህ ፡ መለወጥህ ፡ በጣም ፡ ነው ፡ የገረመን በማለት ፡ ጥያቄ ፡ ለእኔ ፡ ሲያቀርቡ ብር ፡ ወርቅም ፡ አይደለም ፡ አንድ ፡ ነው ፡ ምስጢሩ ኢየሱሱ ፡ እየሱስ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (X ፪) ሰላሜማ ፡ ደስታዬማ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ለኔ ምንም ፡ ነገር ፡ የማይተካው ፡ ነው ፡ የዘላለሜ (ሳየው ፡ ካጎነበስኩበት ፡ ሳየው ፡ ቀና ፡ ቀና ፡ እላለሁ ሳየው ፡ ምርኮ ፡ እንዳገኘ ፡ ሰው ፡ በፊቱ ፡ እዘላለሁ) ፡ X ፪ ሳየው ሳየው ሳየው ሳየው ፡ (X ፪) ሰው ፡ አለኝ ፡ ቢለኝ ፡ የእርካታ ፡ ምንጭ የደስታ ፡ ምንጭ ፡ ልክ ፡ ነው ፡ እሱማ ከአምላኬ ፡ አይበልጥም ፡ አንጂ ፡ ከኢየሱስ ፡ አይበልጥም ፡ እንጂ (X ፫)