Loading
Singer
ሳመልክህ ፡ እንድኖር ፡ ውስጤ ፡ ሳይል ፡ ዝም ምነው ፡ ቀኑ ፡ ባይኖር ፡ ሌቱም ፡ ባይጨልም መንፈሱን ፡ ፈልጌ ፡ ተዘልዬ ፡ እኔማ ሰከንዷም ፡ አትለፍ ፡ ድምጼ ፡ ሳይሰማ (፪x) አዝ፦ እኔማ ፡ እንዴት ፡ ችዬ ፡ ዝም እኔማ ፡ አምልኮዬ ፡ አይቆም (፪x) ጌታዬ ፡ መጣና ፡ እንባዬን ፡ አየና ነገሬን ፡ ፈወሰው ፡ የልቤ ፡ ደርሰ አይደለም ፡ ከሩቅ ፡ አለሁ ፡ ባዬ እንዲህ ፡ ነው ፡ ሲሰራ ፡ ጌታዬ (፪x) እንዳሰብኩት ፡ ባይሆን ፡ (ይሁና ፡ አዋቂ ፡ ነውና) የልቤ ፡ ባይሞላ ፡ (ይሁና ፡ አዋቂ ፡ ነውና) መልሴ ፡ ቢዘገይም ፡ (ይሁና ፡ አዋቂ ፡ ነውና) ቅትር ፡ ላይ ፡ ቢጨልም ፡ (ይሁና ፡ አዋቂ ፡ ነውና) ምክንያቴን ፡ ጥዬ ፡ ሰበቤን ፡ ትቼ አመልካለሁኝ ፡ አምላክ ፡ አግኝቼ (፪x) ሳመልክህ ፡ እንድኖር ፡ ውስጤ ፡ ሳይል ፡ ዝም ምነው ፡ ቀኑ ፡ ባይኖር ፡ ሌቱም ፡ ባይጨልም መንፈሱን ፡ ፈልጌ ፡ ተዘልዬ ፡ እኔማ ሰከንዷም ፡ አትለፍ ፡ ድምጼ ፡ ሳይሰማ (፪x) አዝ፦ እኔማ ፡ እንዴት ፡ ችዬ ፡ ዝም እኔማ ፡ አምልኮዬ ፡ አይቆም (፪x) እረስቶታል ፡ አሉ ፡ (ይበሉ ፡ ይፈጸማል ፡ ቃሉ) አባትነቱ ፡ የታል ፡ (ይበሉ ፡ ይፈጸማል ፡ ቃሉ) ህልሜን ፡ ህልም ፡ ቢሉት ፡ (ይበሉ ፡ ይፈጸማል ፡ ቃሉ) ሆኖ ፡ እስከሚያዩት ፡ (ይበሉ ፡ ይፈጸማል ፡ ቃሉ) ምክንያቴን ፡ ጥዬ ፡ ሰበቤን ፡ ትቼ አመልካለሁኝ ፡ አምላክ ፡ አግኝቼ (፪x) ኢየሱሴ ፡ መጣና ፡ እንባዬን ፡ አየና ነገሬን ፡ ፈወሰው ፡ የልቤ ፡ ደርሰ አይደለም ፡ ከሩቅ ፡ አለሁ ፡ ባዬ እንዲህ ፡ ነው ፡ ሲሰራ ፡ ጌታዬ (፪x) አዝ፦ እኔማ ፡ እንዴት ፡ ችዬ ፡ ዝም እኔማ ፡ አምልኮዬ ፡ አይቆም (፪x)