Loading
Singer
እስከሚያውቁኝ ፡ የተጣሉኝ ፡ ሁሉ አስፍቶኛል ፡ ጌታ ፡ እንደ ፡ ቃሉ እኔም ፡ በዝቻለሁ ፡ ደስ ፡ ብሎኛል ፍሬዬም ፡ አብቦ ፡ ይሄው ፡ ይታያል እንዲያ ፡ ያሳደዱኝ ፡ ጠላቶቼ ለመሆን ፡ ፈለጉ ፡ ወዳጆቼ እርሆቦት ፡ ጌታ ፡ ስላሰኘኝ እግዚአብሔር ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ነው ፡ አለኝ አዝ፦ ሮሆቦት (፪x) ፡ እግዚአብሔር ፡ አስፍቶልኛል መሻቴንም ፡ ፈጽሞልኛል (፪x) የገባልኝን ፡ ቃል ፡ እይፈጽምም ብዬ ፡ ተናግሬ ፡ ከቶ ፡ አይሆንም ባልኩኝ ፡ ጊዜ ፡ እግዚአብሔር ፡ ትቶኛል ርሆቦት ፡ ጌታ ፡ አስፍቶልኛል ዛሬ ፡ አቁሞኛል ፡ በተራራ አሳልፎ ፡ ያንን ፡ ሁሉ ፡ መከራ እኔም ፡ እነግራለሁ ፡ በረከቴን ያደረገልኝን ፡ መድሃኔቴን አዝ፦ ሮሆቦት (፪x) ፡ እግዚአብሔር ፡ አስፍቶልኛል መሻቴንም ፡ ፈጽሞልኛል (፪x) አሁን ፡ ግን ፡ ጽዋዬ ፡ ተርፎልኛል እስክረሰርስ ፡ ድረስ ፡ ሞልቶልኛል ከእንግዲህ ፡ በኋላ ፡ ከቶ ፡ አልጐድልም በረከት ፡ አድርጐኛል ፡ ለዚህ ፡ ዓለም የገባልኝን ፡ ቃል ፡ አይፈጽምም ብዬ ፡ ተናግሬ ፡ ከቶ ፡ አይሆንም ባልኩኝ ፡ ጊዜ ፡ እግዚአብሔር ፡ ትቶኛል ርሆቦት ፡ ጌታ ፡ አስፍቶልኛል አዝ፦ ሮሆቦት (፪x) ፡ እግዚአብሔር ፡ አስፍቶልኛል መሻቴንም ፡ ፈጽሞልኛል (፪x)