Loading
Singer
ዓይኖቼን ፡ አነሳሁ ፡ ወደ ፡ ተራሮቹ ይረዱኝ ፡ እንደሆን ፡ ብዬ ፡ ትልቆቹ ታግሼ ፡ ጠበኩኝ ፡ የቃል ፡ ተስፋቸውን ዛሬ ፡ ነገ ፡ እያልኩኝ ፡ ሳይ ፡ እጅ ፡ እጃቸውን ክረምት ፡ አልፎ ፡ በጋ ፡ ይኸው ፡ መጣ ረዳቴ ፡ ግን ፡ ከየት ፡ ከየት ፡ ይምጣ አቤቱ ፡ ጌታዬ ፡ አድነኝ በደጅህ ፡ መጣሁኝ ፡ መረጥኩኝ (፪x) ረድኤቴ ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ዘንድ ፡ ነው ሰማይን ፡ ምድርን ፡ ከሰራው (፪x) እግዚአብሔር ፡ ደግ ፡ ነው ፡ አያሳፍርም ይረዳኛል ፡ አምናለሁ ፡ አያሳፍርም የጨለመ ፡ ቢመስልም ፡ አያሳፍርም ጌታ ፡ ይመጣል ፡ አይቀርም ፡ አያሳፍርም (፪x) ዓይኖቼን ፡ ቀና ፡ አድርጌ ፡ ያልከኝን ፡ አስታውሳለሁ መከራዬን ፡ ሀዘኔን ፡ ያን ፡ ጊዜ ፡ እረሳዋለሁ (፪x) እዛ ፡ ጋር ፡ አለው ፡ ዋጋ (፪x) አንተ ፡ ጋር ፡ አለው ፡ ዋጋ እዛ ፡ ጋር ፡ አለው ፡ ዋጋ