Loading
Singer
እንዳላየ በሚያልፍበት - የከበበኝ ይህ ሁሉ ሰው በሞት ጥላ ስር ካለሁበት - እግዚአብሔር ነው የደረሰው! [አዝ] “በችግሩ - ‘እግዚአብሔር ሆይ’ - ለምን ይላል - በደረቁ” “አላየዉም - አልሰማዉም” - ብለው ሳቁ ተሳለቁ! አምላኬ ግን - አልሰጠኝም - ለሳቁብኝ አሳልፎ ድካሞቼን - አስወገደ - እንደጊዜው አረጋግፎ! [አዝ] ብዙ ሰልፎች - በነፍሴ ላይ - ሲንጓደዱ እየዋሉ አልፎኝ ሄዷል ብዙ ጊዜ - ከንፈር መጦ ሰው ላመሉ! “ማን ያድነኝ?” ባልኩት ጩኸት - ይነግዳል ግብዝ መንጋ በዙሪያዬ ካሉ እጆች - የ’ሱ ብቻ ተዘረጋ! [አዝ] ትናንትና በደም ገንዝብ - ኑሮ አቁመው የደመቁ አሁን የሉም ጠፋፍተዋል - እንደጤዛ አየደረቁ! ለምለም መሳይ የጊዜያዊ - መንገዶችን በለመዱ ዛሬ አልቀናም ተምሬያለሁ - እሄዳለሁ በመንገዱ! [አዝ] የሰው ልቡ ይታበያል - መነሻዉን እየረሳ ቀን ሲያልፍለት እድል ሲያገኝ - የወደቀን አያነሳ! በመከራ መሸሸጊያ - በክፉ ቀን የሚጠራ እግዚአብሔር ነው ፈጥኖ ደራሽ - እንደጊዜው የሚሰራ! [አዝ]