Loading
Singer
ከእግርህ ፡ ስር ፡ ሆኜ ፡ ልማር ፡ ቃልህን ከእግርህ ፡ ስር ፡ ሆኜ ፡ ልወቅ ፡ ቃልህን ረቢ ፡ ሆይ(፪) (ረቢ ፡ ሆይ) ፡ ና ፡ አስተምረኝ (ረቢ ፡ ሆይ) ፡ በቃልህ (ረቢ ፡ ሆይ) ፡ መንገዴን ፡ አቅና (ረቢ ፡ ሆይ) ፡ ከሕይወት ፡ ቃልህ(፪) ቃልህ ፡ ለመንገዴ ፡ ለሕይወቴ ፡ ብርሃን ፡ ነው ይህን ፡ ክፉ ፡ ዘመን ፡ የማልፈው ፡ በአንተ ፡ ነው በሚገባኝ ፡ መንገድ ፡ ና ፡ አስተምረኝ የሕይወትን ፡ መንገድ ፡ አቅጣጫን ፡ አሳየኝ(፪) ቃልህ ፡ ይብራልኝ ፡ ጌታ(፪) እንድኖር ፡ ሁሌ ፡ በእርጋታ ቃልህ ፡ ይብራልኝ ፡ ጌታ(፪) ቃልህን ፡ ያገኘ ፡ ልቦናው ፡ ይበራል ጥበብ ፡ እያበዛ ፡ በክብር ፡ ይዘልቃል ጥፋት ፡ አያገኘው ፡ ሕይወት ፡ የሚገታ እርስቱን ፡ ይወርሳል ፡ የማታ ፡ የማታ(፪) ቃልህ ፡ ይብራልኝ ፡ ጌታ(፪) እንድኖር ፡ ሁሌ ፡ በእርጋታ ቃልህ ፡ ይብራልኝ ፡ ጌታ(፪) ከእግርህ ፡ ስር ፡ ሆኜ ፡ ልማር ፡ ቃልህን ከእግርህ ፡ ስር ፡ ሆኜ ፡ ልወቅ ፡ ቃልህን ረቢ ፡ ሆይ(፪) (ረቢ ፡ ሆይ) ፡ ና ፡ አስተምረኝ (ረቢ ፡ ሆይ) ፡ በቃልህ (ረቢ ፡ ሆይ) ፡ መንገዴን ፡ አቅና (ረቢ ፡ ሆይ) ፡ ከሕይወት ፡ ቃልህ(፪)