Loading
ቆጠርከኝ ፡ እንደ ፡ ባለማዕረግ ሳልለፋ ፡ ምንም ፡ ሳላደርግ ምህረትህ ፡ በዝቶልኝ ፡ በላዬ ኧረ ፡ ደግ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ ልናገር ፡ እኔስ ፡ ቸርነትህን አላውቅም ፡ ክፉ ፡ መሆንህን (፪x) እኔማ ፡ ይገርመኛል ፡ ሁልጊዜ ፡ ይደንቀኛል እኔማ ፡ ይገርመኛል ፡ ሳስበው ፡ ይደንቀኛል ሹመት ፡ ሆኖልኝ ፡ ነው ፡ ከዓለም ፡ የተወሰነ ማንም ፡ የማይቀያይረው ፡ ከላይ ፡ የሆነ ልጄ ፡ ነህ ፡ ብሎኛል ፡ ምን ፡ ልበል ፡ ይህ ፡ ማዕረጌ ፡ ነው ውስጤን ፡ መደነቅ ፡ ሞልቶታል ፡ ለእኔ ፡ በሆነው እኔማ ፡ ይገርመኛል ፡ ሁልጊዜ ፡ ይደንቀኛል እኔማ ፡ ይገርመኛል ፡ ሳስበው ፡ ይደንቀኛል አዝ፦ ቆጠርከኝ ፡ እንደ ፡ ባለማዕረግ ሳልለፋ ፡ ምንም ፡ ሳላደርግ ምህረትህ ፡ በዝቶልኝ ፡ በላዬ ኧረ ፡ ደግ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ ልናገር ፡ እኔስ ፡ ቸርነትህን አላውቅም ፡ ክፉ ፡ መሆንህን በህልሜ ፡ በእውኔ ፡ አስቤ ፡ የማላውቀውን ብዙ ፡ አድርገህልኛል ፡ ያልጠበኩትን ልዘምር ፡ በገናዬን ፡ ላንሳ ፡ ቅኔን ፡ ልደርድር ግሩምና ፡ ድንቅ ፡ የሆነውን ፡ ስራህን ፡ ልናገር እኔማ ፡ ይገርመኛል ፡ ሁልጊዜ ፡ ይደንቀኛል እኔማ ፡ ይገርመኛል ፡ ሳስበው ፡ ይደንቀኛል ቆጠርከኝ ፡ እንደ ፡ ባለማዕረግ ሳልለፋ ፡ ምንም ፡ ሳላደርግ ምህረትህ ፡ በዝቶልኝ ፡ በላዬ ኧረ ፡ ደግ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ ልናገር ፡ እኔስ ፡ ቸርነትህን አላውቅም ፡ ክፉ ፡ መሆንህን አይቆጠር ፡ እንዲሁ ፡ አይባል ፡ ቸርነትህ የማይለወጠው ፡ ፍቅርህ ፡ የአባትነትህ ኧረ ፡ እንዴት ፡ ብዬ ፡ እገልጸዋለው ፡ ያረክልኝን ከቁጥር ፡ በላይ ፡ የበዛው ፡ የዋልክልኝን እኔማ ፡ ይገርመኛል ፡ ሁልጊዜ ፡ ይደንቀኛል እኔማ ፡ ይገርመኛል ፡ ሳስበው ፡ ይደንቀኛል ቆጠርከኝ ፡ እንደ ፡ ባለማዕረግ ሳልለፋ ፡ ምንም ፡ ሳላደርግ ምህረትህ ፡ በዝቶልኝ ፡ በላዬ ኧረ ፡ ደግ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ ልናገር ፡ እኔስ ፡ ቸርነትህን አላውቅም ፡ ክፉ ፡ መሆንህን
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.