Loading
Singer
ዘምሬ፡ስወርድ: ሰው: ጎሽ ፡ እንዲለኝ ስሜን ፡ አክብሮ ፡ እንዲያሞግሰኝ ፍፁም ፡ አልሻም ፡ ደምቆ ፡ መታየት ክብርህን ፡ ጋርዶ ፡ እራስን ፡ መግለጽ እኔ ፡ ውርንጫ : ነኝ ፡ ጌታዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው እርሱን ፡ አክብሩልኝ ፡ ለእኔ ፡ ክብሬ ፡ ይሄ ፡ ነው ኤፍታህ: ያለኝ ፡ ጌታ ፡ ለክብሬ ፡ አይደለም እርሱን ፡ ላከብር ፡ እንጂ ፡ ልዘምር ፡ ዘለዓለም መሳሪያ ፡ ድምጼን ፡ የማዋህደው ጌታን ፡ ላከብር ፡ ተመስገን ፡ ልለው አይደለም ፡ ለእኔ ፡ ክብሩ ፡ ለእርሱ ፡ ነው በሕይወቴ ፡ ውስጥ ፡ አለኝ ፡ ውለታው ቆሜ ፡ ምዘምረው ፡ ሱስ ፡ ይዞኝ ፡ አይደለም ፍቅሩ ፡ አሸንፎኝ ፡ ነው ፡ ማርኮኝ ፡ ለዘለዓለም ልምድ ፡ የለኝም ፡ ነበር ፡ የግጥም ፡ የዜማ ግን ፡ ለኢየሱስ ፡ ክብር ፡ ይህ ፡ ሁሉ ፡ ተስማማ (፪x) ሃሳቡን ፡ ይዤ ፡ ላገለግለው የውን ፡ ሃሳቤ ፡ የእንቅልፍ ፡ ህልሜ ፡ ነው ከብሮ ፡ በዓይኔ ፡ ሳይ ፡ ጠግቤ ፡ እረካለው ምግብ ፡ አልሻም ፡ ሆዴን ፡ እረሳለሁ ጌታ ፡ ሲከብርልኝ ፡ ዝለል ፡ ያሰኘኛል ዘምር ፡ በእልልታ ፡ አመስግን ፡ ይለኛል አመስግኜው ፡ ሁሌ ፡ እኔ ፡ አልጠግብምና ገና ፡ እዘምራለሁ ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ እስኪመጣ