Loading
Singer
አዝ፦ ቀንበር ፡ ሰብሮ ፡ እስራትን ፡ የሚፈታ አሃሃሃ ፡ ማን ፡ እንደ ፡ ጌታ ፡ ማን ፡ እንደኢየሱስ ፡ ማን ፡ እንደጌታ ከፍ ፡ የሚያደርግ ፡ አንስቶ ፡ ከውርደት ፡ ቦታ አሃሃሃ ፡ ማን ፡ እንደጌታ ፡ ማን ፡ እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ ማን ፡ እንደጌታ ለዚህ ፡ ጌታ ፡ እሰግድለታለሁ ተሸክሞኝ ፡ እዚህ ፡ ደርሻለሁ ለዚህ ፡ ንጉሥ ፡ እቀኝለታለሁ በእርሱ ፡ ብርታት ፡ ዛሬን ፡ አይቻለሁ ምስኪን ፡ ችግረኛን ፡ እንደማንም ፡ ሳይተው እንደ ፡ ባለማዕረግ ፡ ስፍራን ፡ የሚሰጠው የወደቀን ፡ ማንሳት ፡ ክብር ፡ የሆነለት መታሰቢያም ፡ ሚያቆም ፡ ሰርቶ ፡ ታምራት ባርኮ ፡ እየባረከ ፡ በእርሱ ፡ ደግነት አክብሮ ፡ የሚያኖር ፡ ነው ፡ መልካም ፡ አባት (፪x) አዝ፦ ቀንበር ፡ ሰብሮ ፡ እስራትን ፡ የሚፈታ አሃሃሃ ፡ ማን ፡ እንደ ፡ ጌታ ፡ ማን ፡ እንደኢየሱስ ፡ ማን ፡ እንደጌታ ከፍ ፡ የሚያደርግ ፡ አንስቶ ፡ ከውርደት ፡ ቦታ አሃሃሃ ፡ ማን ፡ እንደጌታ ፡ ማን ፡ እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ ማን ፡ እንደጌታ ለዚህ ፡ ጌታ ፡ እሰግድለታለሁ ተሸክሞኝ ፡ እዚህ ፡ ደርሻለሁ ለዚህ ፡ ንጉስ ፡ እቀኝለታለሁ በእርሱ ፡ ብርታት ፡ ዛሬን ፡ አይቻለሁ ምሕረቱን ፡ አብዝቶ ፡ ሞገስ ፡ የሚሰጥ የጠላትን ፡ ከፍታ ፡ ወስዶ ፡ ሚያስረግጥ በክንፎቹ ፡ ጥላ ፡ ሸሽጎ ፡ የሚያኖር ተማምኖ ፡ ለተራው ፡ ስሙን ፡ የሚያከብር እጅግ ፡ የሚራራ ፡ የበዛ ፡ እርዳታው እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ደግ ፡ አምላክ ፡ ማን ፡ ነው (፪x) አዝ፦ ቀንበር ፡ ሰብሮ ፡ እስራትን ፡ የሚፈታ አሃሃሃ ፡ ማን ፡ እንደ ፡ ጌታ ፡ ማን ፡ እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ ማን ፡ እንደጌታ ከፍ ፡ የሚያደርግ ፡ አንስቶ ፡ ከውርደት ፡ ቦታ አሃሃሃ ፡ ማን ፡ እንደጌታ ፡ ማን ፡ እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ ማን ፡ እንደጌታ ለዚህ ፡ ጌታ ፡ እሰግድለታለሁ ተሸክሞኝ ፡ እዚህ ፡ ደርሻለሁ ለዚህ ፡ ንጉስ ፡ እቀኝለታለሁ በእርሱ ፡ ብርታት ፡ ዛሬን ፡ አይቻለሁ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ይበል ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ይበል ከፍ ፡ ከፍ ፡ ይበል ፡ የእኔ ፡ ወዳጅ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ይበል እንደሱ ፡ ጌታ ፡ እስቲ ፡ የታል (፪x) እንደሱ ፡ ፍቅር ፡ እስቲ ፡ የታል (፪x)