Loading
Singer
Updated 9/4/2026
ጌታ ፡ ነው (፪x) ፡ አሄ ጌታ ፡ ነው ፡ ሊረዳኝ ፡ የደረሰው (፪x) አዝ፦ ቀና ፡ አደረገኝ ፡ ቀና እጄን ፡ በእጆቹ ፡ ያዘኛ ከፍሎ ፡ ባሕሩን ፡ አሻገረኝ እኔስ ፡ በጌታ ፡ አመለጥኩኝ (፪x) አመለጥኩኝ ፡ እኔስ ፡ አመለጥኩኝ (፪x) ጠላቴ ፡ እዚያው ፡ ሰጥሞ ፡ ቀረ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ከበረ አልቻልኩትም ፡ ብዬ ፡ ብዙ ፡ ያስቸገረኝን ከእቅሜ ፡ በላይ ፡ ሆኖ ፡ ተራራ ፡ ያስገፋኝን አንድ ፡ ግዜ ፡ ስጠራው ፡ ቃል ፡ ወጥቶ ፡ ከአፉ የከበቡኝ ፡ ሁሉ ፡ ከአጠገቤ ፡ ጠፉ ፡ ተበተነ ፡ ሰልፉ አዝ፦ ቀና ፡ አደረገኝ ፡ ቀና እጄን ፡ በእጆቹ ፡ ያዘኛ ከፍሎ ፡ ባሕሩን ፡ አሻገረኝ እኔስ ፡ በጌታ ፡ አመለጥኩኝ (፪x) አመለጥኩኝ ፡ እኔስ ፡ አመለጥኩኝ (፪x) ጠላቴ ፡ እዚያው ፡ ሰጥሞ ፡ ቀረ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ከበረ ለምንስ ፡ ልረበሽ ፡ የያዝኩት ፡ ሃይለኛ ወጀቡ ፡ ቢበዛም ፡ አይደለም ፡ ሚተኛ ልረጋጋ ፡ በቃ ፡ ጉልበቴ ፡ አይላላ አጠገቤ ፡ ያለው ፡ አለው ፡ መፍትሄ ፡ መላ አልይ ፡ ወደሌላ (፪x) አዝ፦ ቀና ፡ አደረገኝ ፡ ቀና እጄን ፡ በእጆቹ ፡ ያዘኛ ከፍሎ ፡ ባሕሩን ፡ አሻገረኝ እኔስ ፡ በጌታ ፡ አመለጥኩኝ (፪x) አመለጥኩኝ ፡ እኔስ ፡ አመለጥኩኝ (፪x) ጠላቴ ፡ እዚያው ፡ ሰጥሞ ፡ ቀረ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ከበረ ቀና ፡ አደረገኝ (፪x) ፡ ቀና (፪x) እጄን ፡ በእጆቹ ፡ ያዘና (፪x) ባሕሩን ፡ ከፍሎ ፡ አሻገረኝ (፫x) እኔስ ፡ በውዴ ፡ በጌታዬ ፡ አመለጥኩኝ (፪x) አመለጥኩኝ (፬x) አመለጥኩኝ (፬x)