Loading
Singer
ቀድሞ ፡ ወፉ ፡ ሳይጮህ ፡ ጠዋት ፡ በማለዳ ጌታ ፡ ፈጥኖ ፡ መጣ ፡ ልጆቹን ፡ ሊያነቃ ማን ፡ ይላከኝ ፡ ብሎ ፡ ስራውን ፡ ሊሰራ በጠዋት ፡ ለወደደው ፡ ተሰጠው ፡ አደራ ዓለም ፡ ቀውጢ ፡ ሆና ፡ እጅግ ፡ ተጨንቃለች በል ፡ ስጣት ፡ መድሃኒት ፡ ፈውስ ፡ አታተማለች ፍጠን ፡ ልጄ ፡ አለው ፡ ሳይመሽብህ ፡ ቀኑ መርቆ ፡ ሰደደው ፡ እንዲቀና ፡ መንገዱ ቢነቃም ፡ ማለዳ ፡ እጅ ፡ እግሬን ፡ እያለ ከቤቱ ፡ የወጣው ፡ አርፍዶ ፡ ነበረ ከመንገዱ ፡ ሳለ ፡ ገና ፡ ሳያጋምስ ጠለቀበት ፡ ጀምበር ፡ ከቦታው ፡ ሳይደርስ መራመድ ፡ ቢጀምር ፡ ብርሃኑ ፡ ጨላልሞ ተሰብሮ ፡ ወደቀ ፡ መልዕክቱን ፡ አንግቦ ምን ፡ ይጠቅመው ፡ ታዲያ ፡ በጸጸት ፡ መንደዱ መሮጡ ፡ በበጀው ፡ ብሩህ ፡ ሳለ ፡ ቀኑ አዝ፦ ቀን ፡ ሳለ ፡ ልሩጥ ፡ ሳይጨልም ፡ ብርሃኑ ሳይመጣ ፡ ጽልመቱ ፡ ሳይዘኝ ፡ ድባቡ (ልሩጥ) ወገግ ፡ ሲል ፡ ቀኑ (ልሩጥ) ሳይጠልቅ ፡ ጀምበሩ (ልሩጥ) ሳይደክም ፡ ጉልበቴ (ልሩጥ) ሳይዝል ፡ ሰውነቴ ሳይደክም (ልሩጥ) ፡ ጉልበቴ ሳይዝል ፡ ሰውነቴ ሳይመጣ (ልሩጥ) ፡ ጽልመቱ ሳይዘኝ ፡ ድባቡ ትንፋሽ ፡ ያለው ፡ ፍጥረት ፡ መሽቶለት ፡ ሲነጋ አለው ፡ ብዙ ፡ ተግባር ፡ ዛሬን ፡ እንዲተጋ አለው ፡ ብዙ ፡ ልፋት ፡ አለው ፡ ብዙ ፡ ጥረት ነገም ፡ ሌላ ፡ ቀን ፡ ነው ፡ ሌላ ፡ ደግሞ ፡ ሂደት ሳይተጉበት ፡ ዛሬ ፡ ሳይኖሩ ፡ ለዛሬ አንዳች ፡ ሳይጨበጥ ፡ ሲገፋ ፡ ያ ፡ ዕድሜ ምን ፡ ሊፈይድ ፡ ታዲያ ፡ በጸጸት ፡ መንደዱ መሮጡ ፡ ይበጃል ፡ ምቹ ፡ ሳለ ፡ ቀኑ አዝ፦ ቀን ፡ ሳለ ፡ ልሩጥ ፡ ሳይጨልም ፡ ብርሃኑ ሳይመጣ ፡ ጽልመቱ ፡ ሳይዘኝ ፡ ድባቡ (ልሩጥ) ወገግ ፡ ሲል ፡ ቀኑ (ልሩጥ) ሳይጠልቅ ፡ ጀምበሩ (ልሩጥ) ሳይደክም ፡ ጉልበቴ (ልሩጥ) ሳይዝል ፡ ሰውነቴ ሳይደክም (ልሩጥ) ፡ ጉልበቴ ሳይዝል ፡ ሰውነቴ ሳይመጣ (ልሩጥ) ፡ ጽልመቱ ሳይዘኝ ፡ ድባቡ "እራሱን ፡ የሚወቅስ ፡ እራሱንም ፡ ሚዘልፍ ስንቱ ፡ ነው ፡ በቤቱ ፡ እለት ፡ በእለት ፡ ሲያልፍ ዛሬ ፡ የትላንት ፡ ውጤት ፡ መሆኑ ፡ ሚገባው አንዳንዱ ፡ ዘግይቶ ፡ በረፋዱ ፡ ላይ ፡ ነው እንግዲያው ፡ በቀረው ፡ በተረፈው ፡ ዘመን ኋለእኛው ፡ ይበርታ ፡ ይበቀል ፡ ትናንትን የወደቀ ፡ ይነሳ ፡ ይሆን ፡ አዲስ ሃይልን ፡ በሚሰጠው ፡ በእግዚአብሔር ፡ መንፈስ"