Loading
Singer
ያሰቡት ፡ ሳይሰምር ፡ ሲቀር ፡ ሆኖ ፡ እንደህልም በእኩለ ፡ ቀንም ፡ ላይ ፡ በጊዜ ፡ ሲጨልም (፪x) በዕድሜ ፡ ያከማቹት ፡ በዋዛ ፡ ሲበተን በመከራ ፡ እሳት ፡ ማንነት ፡ ሲፈተን (፪x) ሁኔታውን ፡ ሳይሆን ፡ ቃልህን ፡ አምናለሁ ታድናለህ ፡ ብዬ ፡ ስንቴ ፡ ዘምሬያለሁ ወጀቡ ፡ ቢበዛም ፡ በአንተ ፡ ተስፋ ፡ አልቆርጥም ይዘንባል ፡ እላለሁ ፡ ደመናውን ፡ ባላይም አዝ፦ (ቀን ፡ አለ) ፡ ፀሐይ ፡ ትወጣለች (ቀን ፡ አለ) ፡ ይኸ ፡ ሌሊት ፡ ያልፋል (ቀን ፡ አለ) ፡ የታመንኩት ፡ ጌታ (ቀን ፡ አለ) ፡ በክብሩ ፡ ይመጣል (ቀን ፡ አለ) ፡ ፀጋ ፡ ልኮልኛል (ቀን ፡ አለ) ፡ እሸጋገራለሁ (ቀን ፡ አለ) ፡ በአስጨነቀኝ ፡ እራስ ፡ ላይ (ቀን ፡ አለ) ፡ ቆሜ ፡ እዘምራለሁ (፪x) የሕይወት ፡ ቀመሩ ፡ መውረድና ፡ መውጣት ነፍሴ ፡ ምድረበዳው ፡ ውጊያው ፡ ቢያሰለቻት ዓይኖቼ ፡ ሳይወዱ ፡ ተገደው ፡ ቢያለቅሱ የድል ፡ መዝሙሮቼ ፡ ለዛሬ ፡ ቢረሱ እንደማያልፍ ፡ የለም ፡ ይህን ፡ ቀን ፡ አልፋለሁ ጌታዬ ፡ ሲመጣ ፡ በድል ፡ እወጣለሁ ይህ ፡ ሰው ፡ አበቃለት ፡ ያለው ፡ ጠላቴ ፡ ነው በቆፈረው ፡ ጉድጓድ ፡ ሲወድቅ ፡ አየዋለሁ አዝ፦ (ቀን ፡ አለ) ፡ ፀሐይ ፡ ትወጣለች (ቀን ፡ አለ) ፡ ይሄ ፡ ሌሊት ፡ ያልፋል (ቀን ፡ አለ) ፡ የታመንኩት ፡ ጌታ (ቀን ፡ አለ) ፡ በክብሩ ፡ ይመጣል (ቀን ፡ አለ) ፡ ፀጋ ፡ ልኮልኛል (ቀን ፡ አለ) ፡ እሸጋገራለሁ (ቀን ፡ አለ) ፡ ባስጨነቀኝ ፡ እራስ ፡ ላይ (ቀን ፡ አለ) ፡ ቆሜ ፡ እዘምራለሁ በወይን ፡ ሃረግ ፡ ፍሬ ፡ ቢታጣ ፡ የሚቀመስ ምንም ፡ እንኳን ፡ ዛሬ ፡ ባታፈራ ፡ በለስ (፪x) በጐች ፡ ከማደሪያው ፡ ከበረት ፡ ቢታጡ እርሾችም ፡ ጠውልገው ፡ መብልን ፡ ባይሰጡ (፪x) እኔ ፡ ግን ፡ በእግዚአብሔር ፡ በእርሱ ፡ ደስ ፡ ይለኛል በከፍታዎችም ፡ ላይ ፡ ያራምደኛል በመድሃኒቴ ፡ አምላክ ፡ ሃሴት ፡ አደርጋለሁ ጌታ ፡ እግዚአብሔር ፡ ዘወትር ፡ ሃይሌ ፡ ነው አዝ፦ (ቀን ፡ አለ) ፡ ፀሐይ ፡ ትወጣለች (ቀን ፡ አለ) ፡ ይሄ ፡ ሌሊት ፡ ያልፋል (ቀን ፡ አለ) ፡ የታመንኩት ፡ ጌታ (ቀን ፡ አለ) ፡ በክብሩ ፡ ይመጣል (ቀን ፡ አለ) ፡ ፀጋ ፡ ልኮልኛል (ቀን ፡ አለ) ፡ እሸጋገራለሁ (ቀን ፡ አለ) ፡ ባስጨነቀኝ ፡ እራስ ፡ ላይ (ቀን ፡ አለ) ፡ ቆሜ ፡ እዘምራለሁ (፪x) (ቀን ፡ አለ)