Loading
Singer
አዝ፦ ቅዱስ (፬x) ፡ ኃያል (፬x) ቅዱስ (፬x) ፡ ኃያል (፬x) ለሰራዊት ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔር (፪x) በነጩ ፡ ዙፋን ፡ ተቀምጠሃል አክሊላቸውን ፡ ያወሩልሃል ሁሉን ፡ ፈጥረሃል ፡ ፈቃድህ ፡ ሆኗል እጅግ ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ ማን ፡ ይመስልሃል አዝ፦ ቅዱስ (፬x) ፡ ኃያል (፬x) ቅዱስ (፬x) ፡ ኃያል (፬x) ለሰራዊት ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔር (፪x) መልክህ ፡ እንዲህ ፡ ነው ፡ አንተ ፡ ትልቁ . (1) . ቀስተደመና ፡ ማዕረግህ ፡ ዙሪያህ ከቦ ፡ ይልሃል ፡ ኃያል ፡ ቅዱስ ፡ ነህ አዝ፦ ቅዱስ (፬x) ፡ ኃያል (፬x) ቅዱስ (፬x) ፡ ኃያል (፬x) ለሰራዊት ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔር (፪x) እልፍ ፡ ጊዜ ፡ እልፍ ፡ ሺህም ፡ ጊዜ ፡ ሺህ የምትመለክ ፡ በመላእክትህ በኪሩቤል ፡ ላይ ፡ ምትመላለስ እግዚአብሔር ፡ አምላክ ፡ ዘላለም ፡ ቅዱስ አዝ፦ ቅዱስ (፬x) ፡ ኃያል (፬x) ቅዱስ (፬x) ፡ ኃያል (፬x) የሰራዊት ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔር (፪x) ነገሥታት ፡ ሲያልፉ ፡ ሲለዋወጡ አንተ ፡ ግን ፡ ሕያው ፡ ሁልጊዜ ፡ ብርቱ በቅንድቦችህ ፡ ሰውን ፡ መርማሪ መሳይ ፡ የሌለህ ፡ ተወዳዳሪ አዝ፦ ቅዱስ (፬x) ፡ ኃያል (፬x) ቅዱስ (፬x) ፡ ኃያል (፬x) የሰራዊት ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔር (፪x) ከእስራት ፡ ፈቺ ፡ ቀንበር ፡ ሰባሪ በጽድቅ ፡ ዙፋን ፡ ዘላለም ፡ ኗሪ ማደሪያህ ፡ ቅዱስ ፡ አንተ ፡ ቅዱስ ፡ ነህ ሰማይ ፡ ምድር ፡ ሲያልፍ ፡ በክብር ፡ አለህ አዝ፦ ቅዱስ (፬x) ፡ ኃያል (፬x) ቅዱስ (፬x) ፡ ኃያል (፬x) የሰራዊት ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔር (፮x)