Loading
Singer
ክብሩ ፡ ሰማያትን ፡ ምድርን ፡ ሸፍኗል ለሃያልነቱ ፡ ምን ፡ ቃላት ፡ ይገኛል (፪x) መልአክት ፡ በፊቱ ፡ ሳያቋርጡ ፡ ቅዱስ ፡ ይሉታል ይህ ፡ ቅዱስ ፡ ይህ ፡ ቅዱስ በብዙ ፡ ክብር ፡ በብዙ ፡ ፍርሃት ፡ ይሰግዱለታል ይህ ፡ ቅዱስ ፡ አ ፡ ቅዱስ በሰማይ ፡ ሆኖ ፡ በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ሁሉን ፡ የረታ ይህ ፡ ቅዱስ ፡ አሃ ፡ ቅዱስ የማይለወጥ ፡ የማይቀየር ፡ የክብር ፡ ጌታ ይህ ፡ ቅዱስ ፡ አ ፡ ቅዱስ ፡ አይ ፡ ቅዱስ ፡ ዘለዓለም ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ዘለዓለም (፫x) እንደእግዚአብሔር ፡ የለም ለታረደው ፡ በግ ፡ ኃይል ፡ ክብር ፡ ባለጠግነት ሊቀበልህ ፡ ይገባል ፡ አምልኮ ፡ በረከት (፪x) ሲሉ ፡ መላእክት ፡ በታላቅ ፡ ዜማ ፡ ከሩቅ ፡ ይሰማል ይህ ፡ ቅዱስ ፡ ይህ ፡ ቅዱስ ፍጥረት ፡ በቋንቋው ፡ አሜን ፡ እያለ ፡ ይተባበራል ይህ ፡ ቅዱስ ፡ አሃ ፡ ቅዱስ ለሕያው ፡ ለሆነው ፡ ለነበረ ፡ ለአለ ፡ ለሚመለሰው ይህ ፡ ቅዱስ ፡ አሃ ፡ ቅዱስ አምልኮ ፡ ክብር ፡ ክብር ፡ ምሥጋና ፡ ለእርሱ ፡ ይድረሰው ይህ ፡ ቅዱስ ፡ አሃ ፡ ቅዱስ አይ ፡ ቅዱስ ፡ ዘላለም ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ዘላለም (፫x) እንደእግዚአብሔር ፡ የለም ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ዘላለም (፫x) እንደእግዚአብሔር ፡ የለም