Loading
Singer
Updated 5d ago
ክርስትናን ፡ መኖር ፡ መኖርን ፡ እሻለሁ ጥማቴም ፡ ጸሎቴም ፡ አንተን ፡ ለመምሰል ፡ ነው ፡ ጌታ ተቀድሶ ፡ መኖር ፡ መኖርን ፡ እሻለሁ ፡ አው ጥማቴም ፡ ጸሎቴም ፡ አንተን ፡ ለመምሰል ፡ ነው ፡ አባ እቀደሳለሁ (፫x) ፡ ክብርህን ፡ ላየው ፡ ጌታ እቀደሳለሁ (፫x) ፡ ፊትህን ፡ ላየው ፡ አባ እስኪ ፡ አግዘኝ ፡ አቅም ፡ ስጠኝ ለአንተ ፡ እንድኖር ፡ አስጨክነኝ አስጨክነኝ ፡ አስጨክነኝ አስጨክነኝ ፡ አባ ፡ አስጨክነኝ ፡ አዎ ዓለምን ፡ በጽድቅህ ፡ ስራ ፡ እየኮነንኩኝ ፡ እህ ፡ እይኮነንኩኝ ልኑር ፡ አንተን ፡ ኢየሱሴን ፡ እያስከበርኩኝ ፡ አዎ ፡ እያስከበርኩኝ ቅዱሱ ፡ ስምህ ፡ በእኔ ፡ ስለተጠራ ፡ አባ ፡ ስለተጠራ በእኔ እንዳታፍርብኝ (ስምህን እንዳላሰድብ) ፡ እርዳኝ ፡ አደራ ፡ አዎ ፡ እርዳኝ ፡ አደራ ጉልበት ፡ ስጠኝ ፡ አቅም ፡ ስጠኝ በጽድቅ ፡ እንድኖር ፡ አስጨክነኝ አስጨክነኝ ፡ አስጨክነኝ አስጨክነኝ ፡ አባ ፡ አስጨክነኝ ፡ አዎ ጨለማ ፡ ለዋጣት ፡ ዓለም ፡ ብርሃን ፡ ሆኜ ፡ እህ ፡ ርሃን ፡ ሆኜ ለትውልድ ፡ ምሳሌ ፡ አርገኝ ፡ ልኑር ፡ ጨክኜ ፡ አዎ ፡ ልኑር ፡ ጨክኜ መራራውን ፡ አጣፋጭ ፡ የምድር ፡ ጨው ፡ አርገኝ ፡ አባ ፡ የምድር ፡ ጨው ፡ አርገኝ ሁልጊዜ ፡ የጽድቅህ ፡ ፍሬ ፡ አይታጣብኝ ፡ አዎ ፡ አይታጣብኝ እስኪ ፡ አግዘኝ ፡ አቅም ፡ ስጠኝ ለአንተ ፡ እንድኖር ፡ አስጨክነኝ አስጨክነኝ ፡ አስጨክነኝ አስጨክነኝ ፡ አባ ፡ አስጨክነኝ ፡ አዎ ቅድስና ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ቅድስና (፬x) ለጊዜው ፡ ለሚገኝ ፡ ደስታ ፡ ራሴን ፡ አልሸጥም ፡ አሃ ፡ ራሴምን ፡ አልሸጥም ለኑሮ ፡ ለእንጀራ ፡ ብዬ ፡ አልሸቃቅልም ፡ አዎ ፡ አልሸቃቅልም ይራበኝ ፡ እንጂ ፡ ልጣ ፡ ሁሉ ፡ ይቅርብኝ ፡ አዎ ፡ ሁሉ ፡ ይቅርብኝ ጨክኜ ፡ ላገለግልህ ፡ ወስኛለሁኝ ፡ አዎ ፡ ወስኛለሁኝ እንደልብህ ፡ ልኑርልህ በእኔ ፡ ጌታ ፡ ደስ ፡ ይበልህ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ አሃ ፡ እኖራለሁ ክብርህን ፡ ላይ ፡ ናፍቄያለሁኝ እቀደሳለሁ (፫x) ፡ ክብርህን ፡ ላየው ፡ ጌታ እቀደሳለሁ (፫x) ፡ ፊትህን ፡ ላየው ፡ አባ