Loading
Singer
ኧረ ፡ እንዴት (፫x) ፡ ላምልክህ ኧረ ፡ እንዴት ፡ ልሁንልህ ኧረ ፡ እንዴት ፡ ላስደስትህ ፡ ጌታዬ ኧረ ፡ እንዴት ፡ ልሁንልህ ብዘምር ፡ ባከብርህ ፡ ይሄ ፡ ያረካሃል ወይስ ፡ ብሰብክልህ ፡ የቱ ፡ ይሻልሃል ልወቀው ፡ አምላኬ ፡ ምን ፡ ያስደስትሃል "ልጄ ፡ ሆይ ፡ አዳምጪ" መዘመር ፡ መስበኩ ፡ ማሸብሸብ ፡ መዝለሉ ምን ፡ ያደርግልኛል ፡ መሰዋት ፡ ማብዛቱ የኔ ፡ ልብ ፡ በደስታ ፡ ሃሴት ፡ የሚያደርገው በሁለንተናሽን ፡ ስትቀደሺ ፡ ነው ምታደርጊው ፡ ሁሉ ፡ በፊቴ ፡ ሞገስ ፡ የሚያገኘው ዐይኖቼ ፡ ሁልጊዜ ፡ ሚመለከቱት መንፈሱ ፡ ወደተሰበረው ፡ ትሁት በቃሌ ፡ ወደሚንቀጠቀጥ ፡ ሰዉ በሚፈራኝ ፡ እደሰታለሁ ታዲያ ፡ ይሄ ፡ ካስደሰተህ ታዲያ ፡ ይሄ ፡ ካረካህ ልቀደስልህ ፡ ጌታዬ ፡ ልቀደስልህ ልቀደስልህ ፡ አምላኬ ፡ ልቀደስልህ ያለ ፡ ቅድስና ፡ እግዚአብሔርን ፡ ማየት ፡ አይቻልምና ሁሌ ፡ ልቀደስ ያለ ፡ ቅድስና ፡ እግዚአብሔርን ፡ ደስ ፡ ማሰኘት ፡ አይቻልምና ሁሌ ፡ ልቀደስ በሕይወቴ ፡ አክብሬ ፡ አንተን ፡ አገልግዬ የዓለምን ፡ ምኞት ፡ ኀጢአት ፡ እምቢ ፡ ብዬ በእኔ ፡ ደስ ፡ እንዲልህ ፡ ነውና ፡ አላማዬ እኖርልሃለሁ ፡ በቅድስናዬ (፪x)