Loading
Singer
ወይ ፡ አለማወቄ ፡ መጠንከሩ ፡ ልቤ የተረኩልኝን ፡ ይዤ ፡ አለቅ ፡ ማለቴ እምነት ፡ ከመስማት ፡ ነው ፡ መስማትም ፡ በቃሉ እንደተንተራስኩት ፡ ዘመን ፡ ተቆጠሩ ፀሐይ ፡ ስትጠልቅ ፡ ጥላው ፡ ሲሸሽም ፡ ማታ ጉብዝናው ፡ ካለፈ ፡ ቢደርስልኝ ፡ ጌታ አዝ:- ባለኝ ፡ ይሄ ፡ መልካም ፡ ነገር ቀደም ፡ ቢል ፡ ምን ፡ አለ (፬x) ጥርስ ፡ ከነቀልኩበት ፡ ከአደኩበት ፡ ቤቴ አልለይም ፡ እያልኩ ፡ ከእናት ፡ ከአባቴ ይማህተም ፡ ለውጥ ፡ የማደርግ ፡ መስሎኝ ለካ ፡ የመንግሥት ፡ ነው ፡ ይሄ ፡ መቼ ፡ ገብቶኝ ወደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ግዛት ፡ ፈቅጄ ፡ ብገባ ሰብሮ ፡ ቢያላቅቀኝ ፡ ከዚያ ፡ ከጨለማስ አዝ:- ባለኝ ፡ ይሄ ፡ መልካም ፡ ነገር ቀደም ፡ ቢል ፡ ምን ፡ አለ (፬x) መናኛውም ፡ ከፊት ፡ መልካሙም ፡ ከኋላ እንዲሁ ፡ በደመነፍስ ፡ ነበር ፡ የኔ ፡ ስራ ከዛ ፡ ተረት ፡ ተረት ፡ ሕይወት ፡ ውስጥ ፡ አውጥቶ መንገድ ፡ ቢያስጀምረኝ ፡ ትርጉም ፡ ላለው ፡ ኑሮ ቃሉ ፡ ቢጣፍጠኝ ፡ እንደ ፡ ማር ፡ ወለላ ልቤን ፡ ዘልቆ ፡ ፍቅሩ ፡ ውስጥ ፡ ውስጤ ፡ ቢገባስ አዝ:- ባለኝ ፡ ይሄ ፡ መልካም ፡ ነገር ቀደም ፡ ቢል ፡ ምን ፡ አለ (፬x) በከንቱ ፡ ያለፉት ፡ እነዚያ ፡ ቀኖቼ ሳስበው ፡ ይቆጨኛል ፡ የዛሬን ፡ አይቼ ዓለምን ፡ ሳይቀጫት ፡ ወይ ፡ እርሷ ፡ ሳትቀጨው ብላቴና ፡ ሆኖ ፡ አንተን ፡ ላገኘ ፡ ሰው ምንም ፡ እንደማያቅ ፡ ሞኝ ፡ ነው ፡ ቢሉትም እንደእርሱስ ፡ ብልጥ ፡ የለም ፡ አላስተዋሉትም አዝ:- እውነት ፡ ነው ፡ በጊዜ ፡ የበራለት እርሱ ፡ እድለኛ ፡ ነው (፬x)