Loading
Singer
እኔ ፡ የእርሱን ፡ ላውጋው ፡ የፈጠረኝን እርሱም ፡ ስለእኔ ፡ ሁሉን ፡ ሊያውቅልኝ ስምምነት ፡ አደረኩ ፡ ቃልኪዳን ፡ ገባሁኝ እግዚአብሔርን ፡ ብቻ ፡ ላውቀው ፡ እርሱም ፡ ለእኔ ፡ ሊያውቅልኝ አዝ:- ቃልኪዳን ፡ ገባሁኝ (፪x) እኔ ፡ የእርሱን ፡ ብቻ ፡ ላውቀው እርሱም ፡ ለእኔ ፡ ሊያውቅልኝ (፪x) የሰማሁት ፡ ጥበብ ፡ የተቀበልኩት በፈጠረኝ ፡ ጌታ ፡ ሲታይ ፡ ሞኘነት እስከዛሬ ፡ ለእኔ ፡ አውቄ ፡ የአደኩበት ገባኝ ፡ መልካምነት ፡ ምንም ፡ እንደሌለበት ስለዚህ ፡ ነው ፡ እኔን ፡ በቃ??? ፡ ወሰንኩት አዳኜ ፡ አድርጌ ፡ የተቀበልኩት አዝ:- ቃልኪዳን ፡ ገባሁኝ (፪x) እኔ ፡ የእርሱን ፡ ብቻ ፡ ላውቀው እርሱም ፡ ለእኔ ፡ ሊያውቅልኝ (፪x) ልክ ፡ እንደእረኛ ፡ የሚሄድ ፡ ፊት ፡ ፊቴ ከጐኔ ፡ እንዳላጣው ፡ አብሮኝ ፡ ሁልጊዜ ሳጠፋ ፡ ስሳሳት ፡ ሳለሁ ፡ በድካሜ ዞር ፡ ስል ፡ ምህረቱ ፡ የለ ፡ ከኋላዬ እንደእርሱ ፡ ያለ ፡ አምላክ ፡ ከየት ፡ አገኛለሁ ምህረቱ ፡ አስደናቂ ፡ ለዘለዓለም ፡ ነው አዝ:- ቃልኪዳን ፡ ገባሁኝ (፪x) እኔ ፡ የእርሱን ፡ ብቻ ፡ ላውቀው እርሱም ፡ ለእኔ ፡ ሊያውቅልኝ (፪x) ለእናንተስ ፡ ዕውቀት ፡ ማነው ፡ የነገራቹህ ስለእናንተ ፡ ሕይወት ፡ ጠልቆ ፡ ሚያውቅላቹህ ጠጋ ፡ በሉት ፡ እርሱን ፡ ሩህሩህ ፡ ባሕሪውን የሰዎች ፡ ጥያቄ ፡ ችግር ፡ ሚገባው ከእስትንፋስ ፡ የሚቀርብ ፡ ፍቅርን ፡ የተሞላ ማይሰለች ፡ ወዳጅ ፡ ነው ፡ እመኑበት ፡ ብቻ አዝ:- ቃልኪዳን ፡ አድርጉ ፡ ከእርሱ (፪x) እስከ ፡ መቼም ፡ አይጥላቹህ እርሱ ፡ ይሁን ፡ እረኛቹህ (፪x)