Loading
Singer
ቃልህን ላክ ድምፅህን ላክ - የሰማይ አምላክ ጉባዔያችንን ባርክ መንፈስህን ላክ እጅህን ላክ የሰማይ አምላክ ጉባዔያችንን ባርክ በሙታን ሸለቆ በመቃብር ላለው - ቃልህን ላክ በድካም ደርቆ ከህይወት ለጎደለው - ድምፅህን ላክ እስትንፋስን ሰጥተህ ህያው ልታረገው - ቃልህን ላክ ከጉድጓድ አውጥተህ ዳግም ልታቆመው - ድምፅህን ላክ አዝማች ሽባ እንዲተረተር ዕውር እንዲበራ - መንፈስህን ላክ ድንቅ ታምራትህ ዛሬም እንዲሰራ - እጅህን ላክ ደዌ እንዲፈወስ ቋጠሮ እንዲፈታ - መንፈስህን ላክ አምልኮ እንዲቀርብ ለሰራዊት ጌታ - እጅህን ላክ አዝማች ድንበሬን አስፋልኝ ብሎ ለለመነህ - መንፈስህን ላክ እጅህን በላዬ ላይ አበርታልኝ ላለ - እጅህን ላክ ሊነጋ እስኪያቅላላ ታግሎህ ለጠበቀው - እጅህን ላክ በእውነተኛ ባርኮት እንድትገናኘው - መንፈስህን ላክ አዝማች ገበናውን ደብቆ ሊያዋይህ ለመጣ - ቃልህን ላክ እንቆቅልሽ ይዞ ፍቺውን ግን ላጣ - ድምፅህን ላክ ያንጎዳጉድ ድምፅህ አይከልከል ከሰማይ - ቃልህን ላክ ዛሬም እንደጥንቱ ክብርህ በዚህ ይታይ - ድምፅህን ላክ