Loading
Singer
አስጠጋኝ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ወደ ፡ ጉያህ (፫x) የልብህን ፡ እንዳውቅ ፡ እንድረዳ (፫x) አስጠጋኝ ፡ ወዳጄ ፡ ወደ ፡ ስርህ (፫x) ቃልህን ፡ በልቤ ፡ እንድሰውር ፡ እንዳኖር (፫x) አዝ፦ መገኛ ፡ የእኔ ፡ ሥሬ ፡ ጎሳዬም ፡ ቢሆን ፡ ዘሬ (፪x) ውበቴ ፡ ምለው ፡ ክብሬ ፡ ቃልህ ፡ ነው ፡ ቃሌና ፡ ግብሬ (፪x) ቃልህ ፡ አንተ ፡ ጌታ ፡ አንተም ፡ ቃልህ አለማቱ ፡ ሁሉ ፡ የተገኙብህ ቃልህ ፡ አንተ ፡ ጌታ ፡ አንተም ፡ ቃልህ ሰማይና ፡ ምድሩ ፡ የተገኙብህ አዝ፦ መገኛ ፡ የእኔ ፡ ሥሬ ፡ ጎሳዬም ፡ ቢሆን ፡ ዘሬ (፪x) ውበቴ ፡ ምለው ፡ ክብሬ ፡ ቃልህ ፡ ነው ፡ ቃሌና ፡ ግብሬ (፪x) አምላኬ ፡ በቃልህ ፡ ደስ ፡ ይለኛል (፫x) ብዙ ፡ እንደማረከህ ፡ እንዳገኘህ ፡ ይሰማኛል (፫x) ታመንኩኝ ፡ ተፅናናሁ ፡ ሳስበው (፫x) ውስጤም ፡ ረሰረሰ ፡ ሳስገባው ፡ ስሆነው (፫x) አዝ፦ መገኛ ፡ የእኔ ፡ ሥሬ ፡ ጎሳዬም ፡ ቢሆን ፡ ዘሬ (፪x) ውበቴ ፡ ምለው ፡ ክብሬ ፡ ቃልህ ፡ ነው ፡ ቃሌና ፡ ግብሬ (፪x) ቃልህ ፡ አንተ ፡ ጌታ ፡ አንተም ፡ ቃልህ አለማቱ ፡ ሁሉ ፡ የተገኙብህ ቃልህ ፡ አንተ ፡ ጌታ ፡ አንተም ፡ ቃልህ ሰማይና ፡ ምድሩ ፡ የተገኙብህ አዝ፦ መገኛ ፡ የእኔ ፡ ሥሬ ፡ ጎሳዬም ፡ ቢሆን ፡ ዘሬ (፪x) ውበቴ ፡ ምለው ፡ ክብሬ ፡ ቃልህ ፡ ነው ፡ ቃሌና ፡ ግብሬ (፪x)