Loading
Singer
አዝ፦ በጐርፍ ፡ በነፋስ ፡ አይወሰድም ፡ ቤቴ አስተማማኝ ፡ አለት ፡ ቃል ፡ ነው ፡ መሠረቴ (፪x) ቃል ፡ ነው ፡ መሠረቴ ፡ ቃል ፡ ነው (፬x) በእርሱ ፡ የታመነ ፡ ቤቱ ፡ አለት ፡ ላይ ፡ ነው ነፋሱም ፡ አይገፋው ፡ ወጀብ ፡ አይጥለው ሕያው ፡ የሚሰራ ፡ ቃል ፡ አለኝና አሻግሬ ፡ የማየው ፡ ድል ፡ አለ ፡ ገና አነስተኛ ፡ ቢመስልም ፡ ጅማሬዬ እጅግ ፡ ታላቅ ፡ ይሆናል ፡ ፍጻሜዬ ትምክህቴ ፡ ከላይ ፡ ነው ፡ ከአርያም ነገ ፡ ምን ፡ ይሆናል ፡ ብዬ ፡ አልሰጋም ሳልናወጥ ፡ መቆሜ ፡ ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ደንቆታል የአምላኬ ፡ ሰላም ፡ ወርዶ ፡ ልቤን ፡ ሙሉ ፡ አድርጐታል አወዳደቁ ፡ ታላቅ ፡ መጨረሻው ፡ የከፋ እንደ ፡ አሸዋ ፡ ላይ ፡ ቤት ፡ አይደለም ፡ የኔ ፡ ተስፋ መኖሪያዬ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ለዘለዓለም ፡ ለዘለዓለም (፬x) ፀጋ ፡ ወርዶልኛል ፡ ከአርያም ፡ በፍፁም ፡ ወደኋላ ፡ አልልም ለሰማዩ ፡ ርስቴ ፡ እጋደላለሁ ፡ በአምላኬ ፡ ታምኜ ፡ እወርሰዋለሁ የሚያስጨንቀኝን ፡ በእርሱ ፡ ላይ ፡ ጥዬ ፡ በወደደኝ ፡ ጌታ ፡ ተደላልድዬ እተማመናለሁ ፡ በቃልኪዳኑ ፡ አይርድም ፡ ጉልበቴ ፡ ቢከፋም ፡ ቀኑ አዝ፦ በጐርፍ ፡ በነፋስ ፡ አይወሰድም ፡ ቤቴ አስተማማኝ ፡ አለት ፡ ቃል ፡ ነው ፡ መሠረቴ (፪x) ቃል ፡ ነው ፡ መሠረቴ ፡ ቃል ፡ ነው (፬x) ከመቅደሱ ፡ የወጣ ፡ የወረደ ፡ ከሰማይ እርሱ ፡ ነው ፡ መመኪያዬ ፡ የማዕዘኑ ፡ ድንጋይ በእምነት ፡ የታነጸ ፡ ጥብቅ ፡ ነው ፡ መሠረቴ በሽብር ፡ አይናጋ ፡ አይናወጥም ፡ ቤቴ መኖሪያዬ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ለዘለዓለም ፡ ለዘለዓለም (፬x)