Loading
Singer
አዝ፦ ቃል ፡ ብቻ ፡ ተናገር (፬x) የአንተ ፡ ቃል ፡ ተራሮችን ፡ ዘሎ ፡ ይመጣል (፫x) ቃል ፡ ብቻ ፡ ስትናገር ፡ ያልከው ፡ ይሆናል (፫x) የታመመብኝን ፡ ሰው ፡ አልጋ ፡ ላይ ፡ አስተኝቼ ወደ ፡ አንተ ፡ መጣሁኝ ፡ ሁሉን ፡ ነገር ፡ ትቼ ቃልህ ፡ ዓይን ፡ እንዳለው ፡ ስለተማመንኩኝ መቅደስህ ፡ ገብቼ ፡ ቃልህን ፡ ጠበኩኝ ተነሳ ፡ ከአልጋ ፡ ላይ ፡ ብለህ ፡ እዘዝልኝ ወዲያው ፡ እንደሚነሳ ፡ በቃል ፡ አምናለሁኝ (፪x) አዝ፦ ቃል ፡ ብቻ ፡ ተናገር (፬x) የአንተ ፡ ቃል ፡ ተራሮችን ፡ ዘሎ ፡ ይመጣል (፫x) ቃል ፡ ብቻ ፡ ስትናገር ፡ ያልከው ፡ ይሆናል (፫x) ለሰው ፡ ያልነገርኩት ፡ ማንም ፡ የማያውቀው እንድ ፡ ጉዳይ ፡ አለኝ ፡ አንተ ፡ የምታውቀው አምላክ ፡ ይቻልሃል ፡ ለአንተ ፡ ሁሉ ፡ ነገር ለችግሬ ፡ መውጫ ፡ ስለአዘጋጀህ ፡ በር እስከመቼ ፡ ድረስ ፡ ልሸከም ፡ ጥያቄ ቃል ፡ ብቻ ፡ ተናግረህ ፡ ፍታ ፡ እንቆቅልሼን (፪x) አዝ፦ ቃል ፡ ብቻ ፡ ተናገር (፬x) የአንተ ፡ ቃል ፡ ተራሮችን ፡ ዘሎ ፡ ይመጣል (፫x) ቃል ፡ ብቻ ፡ ስትናገር ፡ ያልከው ፡ ይሆናል (፫x) እኔ ፡ የቀመስኩትን ፡ ሕይወት ፡ ያልቀመሱ በምስራች ፡ ወንጌል ፡ ገና ፡ ያልተደረሱ በቤቴ ፡ ሞልተዋል ፡ አንተን ፡ ያልተረዱ ወደ ፡ ሞት ፡ ጐዳና ፡ ዝምብለው ፡ ሚነዱ ዛሬ ፡ ቃል ፡ ተነገር ፡ እንዲለወጡልኝ ቤቴ ፡ ወንጌል ፡ ይግባ ፡ አንተን/ጌታን ፡ ያግኙልኝ (፪x) አዝ፦ ቃል ፡ ብቻ ፡ ተናገር (፬x) የአንተ ፡ ቃል ፡ ተራሮችን ፡ ዘሎ ፡ ይመጣል (፫x) ቃል ፡ ብቻ ፡ ስትናገር ፡ ያልከው ፡ ይሆናል (፫x) ሰማይና ፡ ምድርን ፡ በቃልህ ፡ አጽንተሃል ሁኑ ፡ ስትል ፡ ሆነው ፡ በአንተ ፡ ተፈጥረዋል ቃልህ ፡ ኃይለኛ ፡ ነው ፡ ስልጣን ፡ የተሞላ ሰይጣንን ፡ የሚጥል ፡ እሳት ፡ ነው ፡ ሚባላ በሕይወቴ ፡ ዘመን ፡ የሚያስቸግረኝን ቃል ፡ ብቻ ፡ ተናግረህ ፡ ጠላቴን/ሰይጣንን ፡ ጣልልኝ (፪x) አዝ፦ ቃል ፡ ብቻ ፡ ተናገር (፬x) የአንተ ፡ ቃል ፡ ተራሮችን ፡ ዘሎ ፡ ይመጣል (፫x) ቃል ፡ ብቻ ፡ ስትናገር ፡ ያልከው ፡ ይሆናል (፫x) ደረቁን ፡ ምድረበዳ ፡ ምን ፡ ተስኖት ይሞላዋል ፡ በአበባ ፡ ምን ፡ ተስኖት የጐደለንን ፡ ሁሉ ፡ ምን ፡ ተስኖት ያደርግልናል ፡ ሙሉ ፡ ምን ፡ ተስኖት ለእርሱ ፡ የሚያቅት ፡ የለም ይችላል ፡ እርሱ ፡ ዘለዓለም ሁሉንም ፡ ቻይ ፡ ነውና እናንግሰው ፡ በምሥጋና (፪x) ምን ፡ ተስኖት (፬x) ምን ፡ ተስኖት (፬x) የሞተውን ፡ ሬሳ ፡ ምን ፡ ተስኖት እናያለን ፡ ሲያስነሳ ፡ ምን ፡ ተስኖት ለእኛ ፡ ያቃተን ፡ ሁሉ ፡ ምን ፡ ተስኖት ይቻለዋል ፡ በእርሱ ፡ ምን ፡ ተስኖት ኤልሻዳይ ፡ አምላክ ፡ ነውና የሚሳነው ፡ የለምና ምን ፡ ተስኖት ፡ እንበለው ድል ፡ የሚገኘው ፡ ያኔ ፡ ነው (፪x) ምን ፡ ተስኖት (፬x) ምን ፡ ተስኖት (፬x) ምን ፡ ተስኖት (፬x) ምን ፡ ተስኖት (፬x)