Loading
Singer
ፈውሱን ፡ ፍልጌ ፡ ስንከራተት መፍትሄ ፡ አጥቼ ፡ ስባትት አንዴ ፡ ወደዛ ፡ አንዴ ፡ ወዲህ ፡ ስል እሩጬ ፡ ሩጬ ፡ ልቤ ፡ እስኪዝል ከዚህ ፡ ሁሉ ፡ ጣጣ ፡ የገላገለኝ የዳዊት ፡ ዘር ፡ ነው ፡ ቃልን ፡ የሰጠኝ በአንዲት ፡ ቃል ፡ ብቻ ፡ ተገላገልኩ ተባረክ ፡ ብዬ ፡ አመሰገንኩ አዝ፦ ቃል ፡ አለኝ ፡ በፍፁም ፡ አልወድቅም ቃል ፡ አለኝ ፡ ጌታ ፡ የሰጠኝ (፪x) (ቃል ፡ አለኝ) ፡ በልጅነቴ (ቃል ፡ አለኝ) ፡ ቃል ፡ ገብቶልኛል (ቃል ፡ አለኝ) ፡ እንደማይተወኝ (ቃል ፡ አለኝ) ፡ ጌታ ፡ ነግሮኛል (ቃል ፡ አለኝ) ፡ ከአሁን ፡ በኋላ (ቃል ፡ አለኝ) ፡ የምኖረው (ቃል ፡ አለኝ) ፡ ቃሉን ፡ ከፊቴ (ቃል ፡ አለኝ) ፡ አስቀድሜ ፡ ነው ቃል ፡ አለኝ (፭x) ከጨለማ ፡ ውስጥ ፡ እኔን ፡ የጠራኝ አስደናቂውን ፡ ብርሃን ፡ ያሳየኝ የተናኩትን ፡ ና ፡ ብሎ ፡ ጠርቶ በወንጌል ፡ ዘይት ፡ ራሴን ፡ ቀብቶ የሚያየኝ ፡ ሁሉ ፡ እስኪገረም አቆመኝ ፡ ጌታ ፡ ለምስክር እንደ ፡ መልካሙ ፡ እንደዛ ፡ መሬት ቃሉን ፡ ዘራብኝ ፡ አረኩኝ ፡ ሀሴት አዝ፦ ቃል ፡ አለኝ ፡ በፍፁም ፡ አልወድቅም ቃል ፡ አለኝ ፡ ጌታ ፡ የሰጠኝ (፪x) (ቃል ፡ አለኝ) ፡ በልጅነቴ (ቃል ፡ አለኝ) ፡ ቃል ፡ ገብቶልኛል (ቃል ፡ አለኝ) ፡ እንደማይተወኝ (ቃል ፡ አለኝ) ፡ ጌታ ፡ ነግሮኛል (ቃል ፡ አለኝ) ፡ ከአሁን ፡ በኋላ (ቃል ፡ አለኝ) ፡ የምኖረው (ቃል ፡ አለኝ) ፡ ቃሉን ፡ ከፊቴ (ቃል ፡ አለኝ) ፡ አስቀድሜ ፡ ነው ቃል ፡ አለኝ (፭x) እንደ ፡ አብርሃም ፡ በድንቅ ፡ የጠራኝ ሁሉንም ፡ ተወው ፡ ውጣ ፡ አትፍራ ፡ ያለኝ እስከ ፡ ዓለም ፡ ፍጻሜ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ነው የቃሉ ፡ መንፈስ ፡ በውስጤን ፡ ያለው ስለዚህ ፡ አልፈራም ፡ አልሸበር ድምፅን ፡ ሰማሁኝ ፡ ከእግዚአብሔር ወድቄ ፡ የምቀር ፡ መቼ ፡ ሆንኩና ጌታ ፡ ነግሮኛል ፡ ሄዳልሁ ፡ ገና አዝ፦ ቃል ፡ አለኝ ፡ በፍፁም ፡ አልወድቅም ቃል ፡ አለኝ ፡ ጌታ ፡ የሰጠኝ (፪x) (ቃል ፡ አለኝ) ፡ በልጅነቴ (ቃል ፡ አለኝ) ፡ ቃል ፡ ገብቶልኛል (ቃል ፡ አለኝ) ፡ እንደማይተወኝ (ቃል ፡ አለኝ) ፡ ጌታ ፡ ነግሮኛል (ቃል ፡ አለኝ) ፡ ከአሁን ፡ በኋላ (ቃል ፡ አለኝ) ፡ የምኖረው (ቃል ፡ አለኝ) ፡ ቃሉን ፡ ከፊቴ (ቃል ፡ አለኝ) ፡ አስቀድሜ ፡ ነው ቃል ፡ አለኝ (፭x) (ቃል ፡ አለኝ) ፡ በልጅነቴ (ቃል ፡ አለኝ) ፡ ቃል ፡ ገብቶልኛል (ቃል ፡ አለኝ) ፡ እንደማይተወኝ (ቃል ፡ አለኝ) ፡ ጌታ ፡ ነግሮኛል (ቃል ፡ አለኝ) ፡ ከአሁን ፡ በኋላ (ቃል ፡ አለኝ) ፡ የምኖረው (ቃል ፡ አለኝ) ፡ ቃሉን ፡ ከፊቴ (ቃል ፡ አለኝ) ፡ አስቀድሜ ፡ ነው ቃል ፡ አለኝ