Loading
Singer
አዝ፦ ኦሆሆ ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ ኦሆሆ ፡ በሰማይ እልልታ ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ እልልታ ፡ በሰማይ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ኢየሱስ ፡ ከበረ ፡ በዓለም ፡ ላይ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ኢየሱስ ፡ ነገሠ ፡ በዓለም ፡ ላይ (፪x) የወንጌሉ ፡ ስራ ፡ ድንቅን ፡ አደረገ ጸድቅን ፡ እየዘራ ፡ ፍርድን ፡ አስወገደ ሽባው ፡ ተተርትሮ ፡ እውሩ ፡ ዐይኑ ፡ በራ ምስኪኑ ፡ ከወድቀት ፡ ተነስቶ ፡ እግሩ ፡ ጸና አዝ፦ ኦሆሆ ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ ኦሆሆ ፡ በሰማይ እልልታ ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ እልልታ ፡ በሰማይ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ኢየሱስ ፡ ከበረ ፡ በዓለም ፡ ላይ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ኢየሱስ ፡ ነገሠ ፡ በዓለም ፡ ላይ (፪x) ለነገድ ፡ ለቋንቋ ፡ ተነገረ ፡ አዋጁ ፍቅርን ፡ እንደሰጠን ፡ እግዚአብሔር ፡ በልጁ የምስራቹ ፡ ቃል ፡ ሆነልን ፡ ብርሃን በጨለማ ፡ ያሉ ፡ አዩት ፡ ጌታችንን አዝ፦ ኦሆሆ ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ ኦሆሆ ፡ በሰማይ እልልታ ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ እልልታ ፡ በሰማይ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ኢየሱስ ፡ ከበረ ፡ በዓለም ፡ ላይ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ኢየሱስ ፡ ነገሠ ፡ በዓለም ፡ ላይ (፪x) ቃሉ ፡ እየነጐደ ፡ ምድርን ፡ አለበሰ የዲያቢሎስን ፡ ክንድ ፡ እያፈራረሰ ለኃጢአት ፡ እስረኞች ፡ ክብደት ፡ ጸናባቸው ኢየሱስ ፡ ዋስ ፡ ሆነና ፡ ነፃ ፡ ለቀቃቸው አዝ፦ ኦሆሆ ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ ኦሆሆ ፡ በሰማይ እልልታ ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ እልልታ ፡ በሰማይ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ኢየሱስ ፡ ከበረ ፡ በዓለም ፡ ላይ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ኢየሱስ ፡ ነገሠ ፡ በዓለም ፡ ላይ (፪x)