Loading
Singer
ኦ ፡ የድል ፡ አምላክ ፡ ነህ ፡ ኦ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ኦ ፡ በክብር ፡ ያለህ ፡ ኦ ፡ የጽድቅ ፡ ንጉሥ ኦ ፡ ታላቅ ፡ ማዳንን ፡ ኦ ፡ አርገሃልና ኦ ፡ ለስምህ ፡ ይሁን ፡ ኦ ፡ ክብር ፡ ምሥጋና ሁሉን ፡ የምትገዛ ፡ የሁሉ ፡ ጌታ ፡ ነህ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ጽድቅና ፡ እውነት ፡ ነው ፡ መንገድህ በላይም ፡ በሰማይ ፡ ከፍ ፡ ያለ ፡ ነው ፡ ስምህ ስራህ ፡ ታላቅና ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ በምድር የምይፈራህ ፡ ማን ፡ ነው ፡ ስምህን ፡ ያማያከብር ስለበደላችን ፡ በደዌ ፡ የደቀቀው ስለሃጥያታችን ፡ መሰዋእት ፡ የሆነው የእግዚአብሔርን ፡ ፈቃድ ፡ በእጁ ፡ ያከናወነው ኢየሱስ ፡ ከነፍሱ ፡ ድካም ፡ ብርሃንን ፡ ያያል ብዙዎችን ፡ አጽዶቆ ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ ይለዋል መጽሐፉን ፡ ዘርገተህ ፡ ማኅተሞቹን ፡ ልትፈታ ይገባሃል ፡ ኢየሱስ ፡ እል ፡ የነሳህ ፡ ጌታ ክብር ፡ ለአንተ ፡ ነው ፡ ሁሉን ፡ ስለረታህ አህዛብም ፡ ሁሉ ፡ በፊትህ ፡ ይሰግዳሉ ለስምህም ፡ ክብር ፡ ይዘምራሉ ታላቅ ፡ ክብሩን ፡ ትቶ ፡ ዝቅ ፡ ዝቅ ፡ ያለው ራሱን ፡ በአምላኩ ፡ ፊት ፡ ባዶ ፡ ያደረገው እስከመስቀልም ፡ ሞት ፡ የታዘዘው ኢየሱስ ፡ ትንሳኤ ፡ ነው ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ብሏል ባባቱ ፡ ቀኝ ፡ አለ ፡ በክብር ፡ ይመጣል