Loading
Singer
ኦ ፡ ምሥጋና ፡ ለጌታ ፡ ኦ ፡ ምሥጋና ፡ ለኢየሱስ ኦ ፡ ምሥጋና ፡ አሜን ፡ ለአምላኬ ፡ ይገባዋልና (፪x) ጠላት ፡ ዙሪዬን ፡ ሲከበኝ ወደ ፡ አምላኬ ፡ አነባሁኝ መብረቁን ፡ ከሰማይ ፡ ላከ የሚያውከኝን ፡ አወክ የሚገፋኝን ፡ እየገፋ ጌታ ፡ ድንበሬን ፡ አሰፋ ያስጨነቀኝ ፡ እስጨነቀ ስሙን ፡ በኔ ፡ ላይ ፡ አደመቀ ጠላት ፡ በቃሉ ፡ ሲያደናግረኝ ከያዝኩት ፡ እውነት ፡ ሊያላቅቀኝ አምላኬ ፡ አይቶ ፡ ሳቀበት ፡ መታሰቢያውን ፡ ሁሉ ፡ አጠፋበት ግራ ፡ ያጋባኝ ፡ ተበተነ እንደ ፡ ገላባ ፡ በነነ ወጥመድ ፡ መንገዴን ፡ ዘርግቶበት በላዩ ፡ ወድቆ ፡ ተያዘበት የክፉውን ፡ ውሸት ፡ ገለበጠ የእግዚአብሔር ፡ እውነት ፡ ተገለጠ በቤቴ ፡ ሰላም ፡ እረፍት ፡ ሆነ የሱስ ፡ በኑሮዬ ፡ ገነነ የሱስ ፡ በልቤ ፡ ስፍራ ፡ ያዘ ንፋሱ ፡ ፀጥ ፡ አለ ፡ ታዘዘ ማህበል ፡ ወጀቡን ፡ ገሰፀው መርከቡን ፡ በሰላም ፡ አስኬደው