Loading
Singer
አዝ፦ ኦ ፡ እኔ ፡ ማነኝ ቤቴስ : ምንድነው (፪x) የሰማዩን ፡ ዜማ ፡ ዝማሬ የፅድቅን ፡ ቅኔ ፡ አውቄ ፡ ተምሬ እንድኖር ፡ ልብህ ፡ የፈቀደው አምላክ ፡ ሆይ ፡ እኔ ፡ ማነኝ ቤቴስ ፡ ምንድነው (፪x) አውቃለሁ ፡ የእኔ ፡ ማንነቴን የትውልድ ፡ ሐረግና ፡ ቤቴን ለዚህ ፡ ልታበቃኝ ፡ የቻልከው ካንተ ፡ የተነሳ ፡ ብቻ ፡ ነው ይገርመኛል ፡ እስካሁን ፡ ድረስ በቤትህ ፡ ቆሜ ፡ ስመላለስ የተከልከኝ ፡ በቅዱስ ፡ ቃልህ ስራህ ፡ ይደንቀኛል ፡ ምህረትህ አዝ፦ ኦ ፡ እኔ ፡ ማነኝ ቤቴስ ፡ ምንድነው የሰማዩን ፡ ዜማ ፡ ዝማሬ የፅድቅን ፡ ቅኔ ፡ አውቄ ፡ ተምሬ እንድኖር ፡ ልብህ ፡ የፈቀደው ጌታ ፡ ሆይ ፡ እኔ ፡ ማነኝ ቤቴስ ፡ ምንድነው (፪x) ቅኔ ፡ ውሃ ፡ አይደል ፡ በነፃ የሚቀዳ ፡ አይደለም ፡ ከጓዳ የሚፈልቅ ፡ እንጂ ፡ ከሆዴ ፡ ውስጥ የማይደርቅ ፡ አረከው ፡ እንደ ፡ ምንጭ ሰው ፡ ፊት ፡ ዘመርኩ ፡ እንጂ ፡ ላንተ ፡ ነው ምስጋና ፡ አምልኮ ፡ የማቀርበው የምትቀበለኝ ፡ አንተ ፡ ነህ ምርጫህ ፡ ተስማምቶኛል ፡ የእኔ ነህ አዝ፦ ኦ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ አመልክሃለሁ ከመረጥከኝ ፡ ዘምሪ ፡ ብለህ ልትሰማው ፡ ድምፄን ፡ ከፈለክ ምስጋና ፡ አምልኮዬን ፡ ከወደድክ በእውነት ፡ እና: በመንፈስ ፡ ሆኜ ላምልክህ ፡ ላክብርህ ፡ ቆሜ ፡ ውዱ ፡ ጌታዬ (፪x) መለወጤን ፡ ሲያዩ ፡ በዓይናቸው የቀደሞው ፡ እየታወሳቸው ሁለት ፡ የሆንኩኝ ፡ መሰላቸው የውስጤንስ ፡ ማን ፡ ባሳያቸው የተከልከኝን ፡ እኔ ፡ አውቃለሁ በፍቅርህ ፡ ገመድ ፡ ታስሬአለሁ አልቆልኛል ፡ ከእንግዲህ ፡ በቃ የፊት ፡ ነው ፡ እርምጃዬ ፡ ከአንተ ፡ ጋ አዝ፦ ኦ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ አመልክሃለሁ ከመረጥከኝ ፡ ዘምሪ ፡ ብለህ ልትሰማው ፡ ድምፄን ፡ ከፈለግክ ምስጋና ፡ አምልኮዬን ፡ ከወደድክ በእውነትና ፡ መንፈስ ፡ ላምልክህ ፡ ቆሜ (፪x)