Loading
Singer
እንደልቡ ፡ ሃሳብህን ፡ ልክ ፡ እንደ ፡ ፈቃዱ ለእርሱ ፡ የተለዩለት ፡ ለአንዱ ፡ ለሰገዱ መስለውት ፡ በመኖር ፡ ጌታን ፡ ላስከበሩ ዋጋ ፡ አለ ፡ ከእርሱ ፡ ዘንድ ፡ ሲመጣ ፡ በክብሩ ስለዚህ ፡ ወገኔ ፡ አስብ ፡ አስተውል በዚህች ፡ ዓለም ፡ ነገር ፡ እንዳትታለል አንድ ፡ ቀን ፡ ወደላይ ፡ በክብር ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ስትሄድ ፡ በደመና ፡ ወደ ፡ አምላክ ፡ እግዚአብሔር የዘለዓለም ፡ ደስታ ፡ የሁልጊዜ ፡ እረፍት ሃዘን ፡ በሌለበት ፡ ደስ ፡ የሚያሰኝ ፡ ገነት ትኖራለህ ፡ በዚያች ፡ ቅድስቲት ፡ ከተማ ስለዚህ ፡ ወገኔ ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ ተስማማ ኑርለት ፡ ኑርለት ፡ ለጌታ ኑርለት ፡ ኑር ፡ እንደሃሳቡ ኑርለት ፡ ኑር ፡ እንደፈቃዱ ያን ፡ ጊዜ ፡ ታያለህ እርሱ ፡ አንተን ፡ መውደዱ እንደፈቃድህ ፡ መኖርን ፡ መኖርን ፡ አስተምረኝ ለሃሳብህ ፡ መኖርን ፡ መኖርን ፡ አለማምደኝ ለፈቃድህ ፡ መኖርን ፡ መኖረን ፡ አስተምረኝ ለሃሳብህ ፡ መኖርን ፡ መኖርን ፡ አለማምደኝ ልኑር (፪x) ፡ ልኑር (፪x) እንደ ፡ ፈቃድህ ፡ ልኑር እንደ ፡ ሃሳብህ ፡ ልኑር ፀጋህ ፡ ይርዳኝ ፡ ጉልበት ፡ ስጠኝ እኔ ፡ አልችልም ፡ ባክህ ፡ አግዘኝ (፪x) አውቀህ ፡ አገልግለህ ፡ አምላክህን ፡ በክብር ሚገባውን ፡ መጽዋት ፡ አቅርብ ፡ ከእግሩ ፡ ስር ከቶ ፡ እንዳትሰማ ፡ የጠላትን ፡ ወሬ ክብርህ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ አስተውል ፡ ወገኔ ለአፍታ ፡ እንዳትዘነጋ ፡ የመቆምህን ፡ ሚስጥር ዛሬን ፡ የማየትህ ፡ በእርሱ ፡ ነው ፡ በእግዚአብሔር ክብርና ፡ ዝና ፡ ሃብት ፡ ስላለህ ፡ ሳይሆን ስለመረጠህ ፡ ሰው ፡ ስለለየህ ፡ አንተን (፪x) ኑርለት ፡ ኑርለት ፡ ለጌታ ኑርለት ፡ ኑር ፡ እንደሃሳቡ ኑርለት ፡ ኑር ፡ እንደፈቃዱ ያን ፡ ጊዜ ፡ ታያለህ እርሱ ፡ አንተን ፡ መውደዱ እንደፈቃድህ ፡ መኖርን ፡ መኖርን ፡ አስተምረኝ ለሃሳብህ ፡ መኖርን ፡ መኖርን ፡ አለማምደኝ ለፈቃድህ ፡ መኖርን ፡ መኖረን ፡ አስተምረኝ ለሃሳብህ ፡ መኖርን ፡ መኖርን ፡ አለማምደኝ ልኑር (፪x) ፡ ልኑር (፪x) እንደ ፡ ፈቃድህ ፡ ልኑር እንደ ፡ ሃሳብህ ፡ ልኑር ፀጋህ ፡ ይርዳኝ ፡ ጉልበት ፡ ስጠኝ እኔ ፡ አልችልም ፡ ባክህ ፡ አግዘኝ (፪x)