Loading
Singer
ጠላቴን ፡ መውደድ ፡ እንድችል ለክፉ ፡ መልካም ፡ እንዳደርግ ብርሃኔ ፡ እንዲበራ በቅንነት ፡ እንድኖር (፪x) አዝ፡ ፡ ንፁህ ፡ ልብን ፡ ፍጠርልኝ ፡ ፍጠርልኝ ፡ እና ባንተ ፡ የታየው ፡ በኔ ፡ እንዲታይ ፡ ጌታ ያለኝን ፡ መስጠት ፡ እንድችል ፍቅርህ ፡ በዝቶ ፡ እንዲገለጥ እውነት ፡ በኔ ፡ እንድትታይ ለሌሎች ፡ ምሳሌ ፡ እንድሆን ፡ (፪x) አዝ፡ ፡ ንፁህ ፡ ልብን ፡ ፍጠርልኝ ፡ ፍጠርልኝ ፡ እና ባንተ ፡ የታየው ፡ በኔ ፡ እንዲታይ ፡ የሱስ ቅንነት ፡ ትግስትን ፡ ለብሼ ፡ ልገኝ ፡ ሁል ፡ ጊዜ ፍቅር ፡ ይሁን ፡ መታወቂያዬ ፡ ጌታ ፡ አንተን ፡ መምሰሌ ፡ /4