Loading
Singer
ያልተማረውን ፡ ተመራማሪ የዚ ፡ ቤት ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ባለዲግሪ ያሞካሹታል ፡ በዘፈናቸው ያቺኑ ፡ ሳንቲም ፡ እንዲሰጣቸው (ኦ) ሆያ ፡ ሆያ ፡ ሆዬ ፡ ሆ (፪x) ይህ ፡ ሆያ ፡ ሆዬ ፡ መልኩን ፡ ቀይሮ ትንቢት ፡ በሚለው ፡ ስም ፡ ተሸፍኖ እውነት ፡ በሚመስል ፡ ፍፁም ፡ ድራማ ተቀነባብሮ ፡ እኛም ፡ ቤት ፡ ገባ አዝ:- ንቃ ፡ ክርስቲያን ፡ ንቃ በሐሰት ፡ ነቢያት ፡ አትዘናጋ (፪x) ሰው ፡ እንደልቡ ፡ ዝሙትን ፡ ሰርቶ በእርኩሰትና ፡ በአመጽ ፡ ተሞልቶ ብለው ፡ ይሉታን ፡ አንተ ፡ ጐበዝ እግዚአብሔር ፡ መጣ ፡ ሊባርክህ (ኦ) ሆያ ፡ ሆያ ፡ ሆዬ ፡ ሆ (፪x) ሰርቆ ፡ አጭበርብሮ ፡ የሚያመጣውን መልካም ፡ ነው ፡ ብሎ ፡ ቢሰጥ ፡ ገንዘቡን የበለጠውን ፡ ደግሞ ፡ እንዲያመጣ አበዛዋለሁ ፡ ይልሃል ፡ ጌታ (ኦ) ሆያ ፡ ሆያ ፡ ሆዬ ፡ ሆ (፪x) ትክክለኛ ፡ ነቢዮች ፡ አሉ የጌታን ፡ ብቻ ፡ የሚናገሩ እነርሱንማ ፡ መች ፡ ሊሰሟቸው ደፍሮ ፡ ይሏቸዋል ፡ ሟርተኛች ፡ ናቸው አዝ:- ንቃ ፡ ክርስቲያን ፡ ንቃ በሐሰት ፡ ነቢያት ፡ አትዘናጋ (፪x) መንፈስ ፡ ቅዱስን ፡ ቃሉ ፡ እንደሚለው ሌባውን ፡ ሌባ ፡ ጨዋ ፡ አይለው አንተ ፡ ያልሆንከውን ፡ ነህ ፡ የሚልህ ሊጠቅም ፡ አይደለም ፡ ነው ፡ ሊገድልህ አዝ:- ንቃ ፡ ክርስቲያን ፡ ንቃ በሐሰት ፡ ነቢያት ፡ አትዘናጋ (፪x) ትክክለኛ ፡ ነቢዮች ፡ አሉ የጌታን ፡ ብቻ ፡ የሚናገሩ እነርሱንማ ፡ መች ፡ ሊሰሟቸው ደፍሮ ፡ ይሏቸዋል ፡ ሟርተኛች ፡ ናቸው አዝ:- ንቃ ፡ ክርስቲያን ፡ ንቃ በሐሰት ፡ ነቢያት ፡ አትዘናጋ (፪x)