Loading
ንጉሥ ፡ ስለወደደው ፡ እንዲህ ፡ ይደረግለታል ንጉሥ ፡ ስላፈቀረው ፡ እንዲህ ፡ ይደረግለታል ንጉሥ ፡ ስለወደደው ፡ ዘንጉ ፡ ይዘረጋለታል ንጉሥ ፡ ስላፈቀረው ፡ ካባ ፡ ይደረብለታል (፪x) እኔን ፡ ስለወደደኝ ፡ ኢየሱስን ፡ ሰጠኝ እኔን ፡ ስላፈቀረኝ ፡ መድኃኒትን ፡ ሰጠኝ እኔን ፡ ስለወደደኝ ፡ አንድ ፡ ልጁን ፡ ሰጠኝ እኔን ፡ ስላፈቀረኝ ፡ አማኑኤልን ፡ ሰጠኝ ንጉሥ ፡ ስለወደደኝ ፡ እኔስ ፡ ዕድለኛ ፡ ነኝ ንጉሥ ፡ ስላከበረኝ ፡ እኔስ ፡ ዕድለኛ ፡ ነኝ ለእኔ ፡ የተደረገው ፡ ብዙ ፡ እኮ ፡ ነው ለእኔ ፡ የተሰራው ፡ ብዙ ፡ እኮ ፡ ነው አንድ ፡ በአንድ ፡ እቆጥራለሁ የእርሱን ፡ መልካምነት ፡ እናገረዋለሁ (፪x) ምን ፡ ያልተደረገ ፡ ያልሆነልኝ ፡ አለ ከኢየሱስ ፡ ጀምሮ ፡ ለእኔ ፡ ያልተሰጠ ከመልካምነቱ ፡ እኔን ፡ አጠገበ ንጉሥ ፡ እኔን ፡ ወዶ ፡ እንዲህ ፡ አደረገ ለእኔ ፡ የተደረገው ፡ ብዙ ፡ እኮ ፡ ነው ለእኔ ፡ የተሰራው ፡ ብዙ ፡ እኮ ፡ ነው አንድ ፡ በአንድ ፡ እቆጥራለሁ የእርሱን ፡ መልካምነት ፡ እናገረዋለሁ (፪x) አክሊል ፡ እንደለበሰ ፡ ያጌጠ ፡ ሙሽራ ሕይወቴ ፡ በደሙ ፡ ታጥባ ፡ አምራ በፊቱ ፡ የመግባትን ፡ ድፍረት ፡ አግኝታለች ለልዑል ፡ እግዚአብሔር ፡ ዛሬ ፡ ታዜምለታለች ቸር ፡ ነው (፪x) ምሕረቱ ፡ ብዙ ፡ ነው ፍቅሩ ፡ የማያልቅ ፡ ነው (፪x) ወደደኝ ፡ አዳነኝ ለክብሩ ፡ እኔን ፡ መረጠኝ (፪x) (ወደደኝ ፡ አዳነኝ ለክብሩ ፡ እኔን ፡ መረጠኝ (፪x))
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.