Loading
Singer
ተናገረኝ እኔም ሰማሁ አምኛለሁ ተቀብዬ እግዚአብሄር ያለው ይሆናል ሌላውን አልሰማም ብዬ2 ሰው እንደሚለኝ አይደለሁም ሁኔታ እንደሚለኝ ኧረ አይደለሁም ቃሉ እንደሚለኝ ነኛ ጌታ እንደሚለኝ ነኛ ሰማይ ነው የኔ መገኛ ልቤ እኮ ያውቀዋል ያውቀዋል ውስጤም ተረድቶታል ተረድቶታል ሌላ ሌላ ሰፊ ክብር ሌላ ሌላ ትልቅ ከፍታ ሌላ ሌላ ያዘጋጀልኝ ሌላ ሌላ አለኮ ጌታ በእኔ ሊሰራ የወደደውን ስላወቅሁኝ3 ለፈቃዱ ለሃሳቡ እጅ ሰጠሁኝ3 እኔማ የራሴ አይደለሁም ተገዝቻለሁ2 በኢየሱስ ደም ተዋጅቻለሁ2 ለዘላለም ተናገረኝ እኔም ሰማሁ አምኛለሁ ተቀብዬ እግዚአብሄር ያለው ይሆናል ሌላውን አልሰማም ብዬ2 ሰው እንደሚለኝ አይደለሁም ሁኔታ እንደሚለኝ ኧረ አይደለሁም ቃሉ እንደሚለኝ ነኛ ጌታ እንደሚለኝ ነኛ ሰማይ ነው የኔ መገኛ በሰነፍ ቃል እኔ ሳላቅማማ ያላዋቂ ወሬም ሳልሰማ ገና ገና እንደ እግዚአብሄር ቃል ገና ገና ይሆንልኛል ገና ገና መቶ እጥፍ ያንተ ይሁን ብሎ ተናግሮብኛል አሜን አሜን