Loading
Singer
አዝ፦ ሕዝብም ፡ ሁሉ ፡ ይሄዳል ፡ በያምላኩ (፪x) አልተለቁም ፡ በሚያልፈው ፡ የተመኩ (፪x) እኛም ፡ ደግሞ ፡ ዘላላም ፡ እንሄዳለን አናፍርም ፡ አንከሰርም ፡ ጌታን ፡ ታምነን አምላካችን ፡ መጠጊያችን (፪x) በመከራ ፡ ረዳታችን (፪x) ቢነዋወጥ ፡ ምድር ፡ በሞላ (፪x) ያድነናል ፡ የእኛስ ፡ ከለላ (፪x) ነገሥታት ፡ ቢቀየሩ ፡ አንዱ ፡ ባንዱ ፡ ቢተካ እፎይ ፡ ብሎ ፡ ላያድር ፡ ውጥረቱ ፡ ላያበቃ ዘመን ፡ ያመጣው ፡ ችግር ፡ ትውልድን ፡ ሲያሸብረው ለፍጥረት ፡ መታመኛ ፡ ጌታ ፡ አለ ፡ ለታመነው አዝ፦ ሕዝብም ፡ ሁሉ ፡ ይሄዳል ፡ በያምላኩ (፪x) አልተለቁም ፡ በሚያልፈው ፡ የተመኩ (፪x) እኛም ፡ ደግሞ ፡ ዘላላም ፡ እንሄዳለን አናፍርም ፡ አንከሰርም ፡ ጌታን ፡ ታምነን አምላካችን ፡ መጠጊያችን (፪x) በመከራ ፡ ረዳታችን (፪x) ቢነዋወጥ ፡ ምድር ፡ በሞላ (፪x) ያድነናል ፡ የእኛስ ፡ ከለላ (፪x) ሰው ፡ ባለው ፡ ምን ፡ ቢኮራ ፡ ዓይኑን ፡ ካምላኩ ፡ አንስቶ (፪x) ቢደገፍ ፡ በሚጠፋው ፡ መገኛውን ፡ ዘንግቶ (፪x) የቆመ ፡ የመሰለው ፡ እንዳይወድቅ ፡ ይጠንቀቅ (፪x) ቢናወጥ ፡ ምድር ፡ ሰማይ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ የሚያዘልቅ (፪x) ሃሌሉያ ፡ ኦ ፡ ሃሌሉያ (፬x)